Addis Zemen (Sep 29, 2026)
በድጋሚ የወጣ የቶዮታ መኪና ፒካፕ 5L ሞዴል 2005 ዕቃ መላዋወጫ ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተየግል ማህበር የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት 5L ቶዮታ ፒካፕ መኪና ሞዴል 2005 መኪና ዕቃ መለዋወጫ ግዥ በግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ እየገለጽን
- ተወዳዳሪዎች በጨረታ ለመወዳደር የሚችሉ ለመሆናቸው የንግድ ፈቃድ፤ የሙያ ማረጋገጫ ሰርተፊኬትና የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ሕጋዊ አካል የተፃፈ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ከዚህ ቀደም ከሠሩባቸው መ/ቤቶች ለሠሩበት ምስክርነት የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃዎችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ጨረታውን 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
5. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ለመወዳደር የሚያስችል ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ፋይናንሻል እና ቴክኒካል በኦርጂናል እና በኮፒ እያንዳንዱ ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማሳረፍና በፖስታ በማሸግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ዋናው መ/ቤት አ.አ 7ኛ ፎቅ ማስገባት አለባቸ።
7. አሸናፊው ድርጅት በአምስት ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶኛ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ የስምምነቱን ውል መፈረም አለበት።
8. የጨረታ መዝጊያው ሰዓት ከደረሰ እና የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
9. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
10. ጨረታው ኢ.አ መስቀል አደባባይ ፊንፊኔ ሕንፃ ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ፋይ/ ግዢ/ንብ/አስ/መምሪያ 7ኛ ፎቅ የሚከፈት ይሆናል።
11. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል።
12 የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ላይ ቀኑ የሥራ ቀን ከሆነ በዕለቱ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በዋናው መ/ቤት አዲስ አበባ ይከፈታል።
13. የጨረታ መዝጊያው ሰዓት ከደረሰ እና የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
14. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፦
- ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ፈንፊኔ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር፦ 011 552 1009/ 011 552 1458/
ፖ.ሣ.ቁ 9515 ፋክስ 011 551 3654
አ/አ
ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር