Be'kur (Sep 28, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ጎንደር /አስ/ዞን/ ከፍ/ፍ/ቤት ለመቤቱ አገልግሎት የሚዉሉ
- ሎት 1. የመ/ቤቱን ስም የሚገልፅ ላይት ቦክስ እና ክሪስታል ሎጎ፣
- ሎት 2. የባለ ጉዳይ ማስተናገጃ ጠረጴዛ (የሚሰራ)፣
- ሎት 3. የግድግዳ ማስዋቢያ ፓኔል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሳተም ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉና በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- በሎት ከጠቅላላ ዋጋ 200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ከጠቅላላ ዋጋው ላይ አንድ በመቶ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ደ/ጐን/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 35 በመቅረብ ማስያዝ ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በፖስታ ውስጥ አሽጐ ማቅረብ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል፤ገንዘቡም ቢጠፋ መ/ቤቱ ሊጠየቅ አይችልም።
- መ/ቤቱ ለመግዛት የሚፈለጉትን እቃዎች አይነት ዝርዝር የያዘ ሠነድ ማስታወቂያዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 35 በመምጣት እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ በ50 (ሃምሳ ብር) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ቢሮ ቁጥር 35 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑም በ15ኛዉ ቀን 11፡30 ላይ ይታሸጋል።
- ተጫራቾች ወይም ተወካዩች ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛዉ ቀን 2፡30 ቢሮ ቁጥር 35 ይከፈታል።
- አሸናፊው ድርጅት የሚመረጠዉ ወይም የሚለዩት በሎት ወይም በጥቅል ዋጋ ነዉ።
- አሸናፊው ድርጅት የአሸነፈዉን እቃ ደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ሰነድ በሚገዙበት ጊዜ ኦሪጅናል እና ኮፒ ፍቃድ በመያዝ ሰነዱን በአካል ወይም በህጋዊ ወኪላቸዉ አማካኝነት ማቅረብ ይገባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 0386 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
የደቡብ ጎንደር /አስ/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት