Addis Zemen (Sep 28, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ
ቁጥር EEP/NP/NCB/04/2019
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተለያዩ ተሽከርካሪ ጎማዎች ግዥ በዘርፉ ከተስማሩ፣ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት (2) አመት የሚቆይ የማዕቀፍ ስምምነት ውል በመግባት ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት(TIN) ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድህረ-ገፅ (e-GP) ላይ የተመዘገቡ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
2, በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
3. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ህንፃ ቁጥር-11 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) የጨረታ ሰነዱን በሚገዛው ድርጅት ስም ወደ EEP Transmission Construction A/C No.1000252665203 Commercial Bank of Ethiopian (CBE) ትራንስፈር በማድረግ በመክፈል እና የጨረታ ሰነዱን ብሎክ-9 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የተለያዩ ተሽከርካሪ ጎማዎች ግዥ የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለየብቻው በሰም በታሽገ ሁለት ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/NP/NCB/04/2019 የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
No.
|
የግዥው አይነት
|
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ
|
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት
|
የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ጎማዎዎች ግዥ
|
ብር 2,000,000.00 (ሁለት ሚሊዩን ብር
|
ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
|
ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
|
5. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-558-0627 መደወል ይችላሉ።
6. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል