የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አክሲዮን ማህበር G+2 መኖሪያ ቤት መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አክሲዮን ማህበር G+2 መኖሪያ ቤት መሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Sep 30, 2026)

ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አክሲዮን ማህበር በብድር የሰጠውን ገንዘብ በብድር ውሉ መሰረት ስላልተከፈለ ባንኩ በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለብድሩ መከፈል ዋስትና/መያዣ እንዲሆን ሥልጣን ባለው አካል በማስመዝገብ ያሳገደውን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ገንዘቡን ወደ ተበዳሪዎች የብድር እዳ ገቢ ለማድረግ ይፈልጋል።ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች ሐራጁ በሚካሄድበት ዕለት ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ በመቅረብ በጨረታው ላይ እንዲሳተፍ ተጋብዟል፡፡

ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም

የንብረት አስያዥ ስም

የንብረት ዓይነት

ቅርንጫፍ

ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ

የካርታ ቁጥር

የቦታ ስፋት

የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር

ጨረታው የሚካሄድበት ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ

ከተማ

ክ/ከተማ

ወረዳ

1

ፒስ ሁለገብ አገልግሎት የኅብረት ሥራ ማህበር

ፒስ ሁለገብ አገልግሎት የኅብረት ሥራ ማህበር

G+2 መኖሪያ ቤት

 

ሀሩፋ

ሻሸመኔ

አለቼ

ዲዳ ቦቄ

OR002052305022

205.44 ካ.ሜ

14,175,805.45

ጨረታው ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት ከ4:00-6:00 ሰዓት የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሻሸመኔ ዲስትሪክት ያለበት ዳንሱሬ ህንፃ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ይካሄዳል።

ተጫራቾች እንዲያውቋቸው

  1. ተጫራቾች ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4(25%) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ስም አሰርተው ይዞ በአድራሻ ቀርበው በመመዝገብ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡ ጨረታውን በድርጅት ስም የሚጫረት ተጫራች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ምዝገባ፣ ንግድ ፈቃድና የድርጅቱን ውክልና እና የታደሰ መታወቂያ ይዞ መቅረብ አለበት።
  2. ጨረታው ከላይ ቀንና ሰዓቱ በተገለፀው መሠረት ባለዕዳዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይካሄዳል፤ ባለዕዳዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ ግን ሐራጁ እነሱ በሌሉበት ቦታ ይካሄዳል።
  3. ንብረቶቹ በሥራ ሰዓት ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ለተ.ቁ 1 ሀሩፋ ቅርንጫፍ በስልክ ቁጥር 0916-14-92-02/0926-90-89-44 ወይም 0911-87-44-59 በመደወል መጎብኘት ይቻላል።
  4. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15(አሥራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ እንዲቀርብ ይደረጋል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል።
  5. የጨረታው አሸናፊ በሕጉ መሠረት ለመንግስት የሚከፈለውን ማንኛውንም የቫትና ታክስ ክፍያ፣ የስም ማዛወሪያ እና ሌሎች ወጪዎችን ከፍሎ ስሙ ወደ እራሱ እንዲዛወር ያደርገል።
  6. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *