Addis Zemen (Oct 02, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ.ጤ.ጣ ለ 01/209
የአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ የ2019 በጀት አመት የ1ኛ ዙር አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ ህትመቶች፣ የህክምና መለዋወጫ እቃዎች፣ መድሀኒቶች፣ ቋሚ እቃዎች፣ የልብስ ስፌቶች፣ የጥገና እቃዎች የአገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እና ህጋዊ ማስረጋጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለውን የዘመኑን ግብር ከፋይና እና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ።
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር የአቅራቢነት ምዝገባ ያለው።
3. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር ሰነዱ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፤ ጨረታው በ11ኛ ቀን 4፡00 ሰአት ታሽጎ በዛው እለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
4. ተጫራቾች ያሸነፉአቸውን እቃዎች ወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ ንብረት ክፍል ሙሉ ወጪውን ችለው ማስረከብ አለባቸው።
5. የጨረታ ማስረከቢያ ብር 2% ከባንክ በተመሰከረ CPO ማስያዝ አለባቸው፤ መሉ ዝርዝር መረጃው ከሰነዱ ላይ መመልከት አለባቸው።
6. ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
7. ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
9. የጨረታ ሰነድ መሰረዝ መደለዝ እና በፍሉድ መንካት አይቻልም።
10. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
11. ተጫራቾች በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ / ማስገባት አለባቸው።
12. ማንኛውም ተጫራች ላቀረበበት እቃ ሲፒኦ ካላሲያዘ ተቀባይነት የለውም።
13. ተጫራቾች የፎቶ ሳምፕሎች ከምሳፕል እቃ ጋር መቅረብ አለባቸው።
14. ጥቃቅን እና አነስተኛ በተደራጁበት መስክ ደብዳቤ አጽፈው የማምጣት ግዴታ አለባቸው።
አድራሻ፡– አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ ከሰሜን ሆቴል ጀርባ ሲ.ሲ ኤፍ ግቢ አጠገብ
ለበለጠ መረጃ ፡– በስልክ ቁጥር 011 125-0744 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ