የእንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2019 በጀት አመት ለስልጠና፣ ለቴክኖሎጂ እና ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የእንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2019 በጀት አመት ለስልጠና፣ ለቴክኖሎጂ እና ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Oct 19, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የእንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2019 በጀት አመት ለስልጠና፣ለቴክኖሎጂ እና ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን

  • ሎት 1. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣
  • ሎት2. የጽህፈት መሳሪያ ፣
  • ሎት3. የህንጻ መሳሪያ ፣
  • ሎት4. ቴክስታይልና ጋርመንት ፣
  • ሎት 5. የጽዳት ዕቃ ፣
  • ሎት6. የእህል ወፍጮ ማቴሪያል እና የእህል ሚዛን በግልጽ ጨረታ ቁጥር 1 አወዳድሮ ለ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ስራ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡

2. የግብር ከፋዩች መለያ ቁጥር (ቲን) የተሰጣቸው እና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. የግዥው መጠን ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. በግብር ዓመቱ ተገቢዉን የታክስ እና የግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡

6. የሚገዙት ዕቃዎች በተጠየቀው ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኪሽን) መሰረት የጨረታ ሰነዱን እንጅባራ ፖ/ቴ/ኮሌጅ የማይመለስ የኢትዩጵያ ብር 100(አንድ መቶ ብር) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ ለሎት1. ብር 20,000፣ ለሎት2. ብር 10,000 ፣ ለሎት 3. ብር 10,000 ፣ ለሎት 4. ብር 10,000 ፣ ለሎት 5. ብር 5,000 ለሎት 6. ብር 10,000 በመሂ/1 ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሃሳብ ማቅረቢያ ቅጹን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ እን/ፖ/ቴ/ኮሌጅ ከግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ሰነዱን በመግዛት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢ.ቁጥር 7 በ11ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም በተደረገው የጨረታ አከፋፈት ሥርዓት ተገዥ ይሆናሉ፡፡

9. ሥለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 227 02 00 በመደወል መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡

10. ኮሌጁ በጨረታው አሸናፊ ላይ 20 በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት አለው፡፡

11. አሸናፊው ድርጅት ለውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

12. የእንጅባራ ፖ/ቴ/ኮሌጅ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም በጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡

13. አሸናፊዉ ድርጅት ያሸነፈውን እቃ በሙሉ በራሱ ወጭ ኮሌጁ ግቢ ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል ፡፡

የእንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ