Reporter (Oct 18, 2026)
የሐራጅ ማስታወቂያ
ብርሃን ባንክ አ.ማ ከባለእዳዎቹ ላይ ለሚፈልገው ገንዘብ በዋስትና የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረትቶች በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ ማክበር ይኖርባቸዋል::
- 1ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን የ1/4 (አንድ አራተኛ) (ሲፒኦ) በብርሃን ባንክ ኢማ ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ::
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን እንዳሸነፈ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ አለበት:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል::
- የንብረቶቹ ጨረታ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ ይከናወናል::
- የጨረታ አሸናፊው በሚገዛው ንብረት ላይ የሚፈለግ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያዎች እና የሊዝ ክፍያዎች ይመለከተዋል::
- መያዣ ሰጪዎች ሐራጁ በሚከናወንበት ቦታ ቀንና ሰዓት መገኘት ይችላሉ:: ባይገኙ ግን ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል::
- በባንኩ ብድር መምሪያ መስፈርት መሰረት እና በተሰጠው ጊዜ ውስጥ የሚፈለግበትን ለሚያሟላ ተጫራች ባንኩ በከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል::
- ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ኘሮግራም አስይዞ ለመጐብኘት ይቻላል::
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው::
የመኖሪያ ቤት እና ኢንዱስትሪ
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪዉ ስም |
የመያዣ ሰጭዉ ስም |
መኖሪያ /የንግድ ቤት የሚገኝበት አድራሻ |
የቦታው ስፋት በካሬ ሜትር |
የንብረቱ አገልግሎት
|
የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
የጨረታ መነሻ ዋጋ
|
ጨረታዉ የሚካሄድበት ቀን እና ለዓት
|
|
1 |
በሪሶ ዱለቻ |
በሪሶ ዱለቻ |
ቡሌ ሆራ ከተማ ጎሮ ጉዲና ቀበሌ |
3000 ካ.ሜ
|
ኢንዱስትሪ
|
BH/3971/B,495/2015
|
5,500,000.00
|
ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-5፡30 |
|
2 |
ታምሬ ሒንካ |
ታምሬ ሒንካ |
ሻሸመኔ ከተማ ደ/ ቦቃ ቀበሌ |
140 ካ.ሜ
|
መኖሪያ ቤት
|
11980
|
2,350,000.00
|
ህዳር 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-5፡30
|
ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 011-6506900 እና 011-6506276 በመደወል መጠየቅ ይቻላል::