Addis Zemen (Oct 21, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 008/2019
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት አስተዳደር ቢሮ በክልሉ ሥር በሚገኙ መናኻሪያዎች አገልግሎት የሚሰጡ ብቃት ያላቸውን የኢቲኬቲንግ ትግበራ ሶፍትዌር አቅራቢ ድርጅትን፣ ማህበርን ወይም ግለሰብን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውለታ ለማሰራት ይፈልጋል፡
በዚሁ መሰረት፡-
|
ሎት ቁጥር
|
የሚገኝበት ዞን |
የመናኻሪያ ብዛት
|
አገልግሎት የሚሰጠው መናኻሪያ
|
|
1 |
ወላይታ ዞን
|
6 |
ቦዲቲ፣ አረካ፣ ሁምቦ፣ ጉኑኖ፣ ገሱባ እና በሌሀዋሳ
|
|
2 |
ጋሞ ዞን
|
5 |
ሰላምበር፣ ጨንቻ፣ ዋጁፎ፣ ገረሴ እና ብርብር
|
|
3 |
ጌዲኦ ዞን
|
4 |
ይ/ጨፌ ገደብ፣ ጩርሶ እና ወናጎ
|
|
4 |
አሪ ዞን
|
1 |
ጂንካ
|
|
5 |
ኮንሶ |
1 |
ካራት
|
1.ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ አመታዊ የስራ ግብር የከፈሉበትን፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ አያይዘው ጨረታ ሰነድ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
2 ተጫራቾች የሥራውን ዝርዝር እስፔስፍኬሽንና የጨረታ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 17 ድረስ መጥተው የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት /Lot/ 1,2 እና 3 ለእያንዳንዱ 50,000 (ሀምሳ ሺህ) ብር እና ለሎት /Lot/ 4 እና 5 ለእያንዳንዱ 20,000 /ሃያ ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ወይም ባንክ ጋራንቲ በቴክኒካል ኦርጀናል ሰነድ ውስጥ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካል አንድ ኦርጀናልና ሁለት ኮፒ፣ ፋይናንሻል አንድ ኦርጀናልና ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸውን ለየ ብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና ጠቅላላውን በአንድ በእናት ፖስታ ታሽጎ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 11፡30 ድርስ ቢሮው ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች ሶፍትዌር ልማት ማረጋገጫ እና የሶፍትዌር ደህንነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ የተቀመጡ ሌሎች ዝርዝር መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው፡፡
7. ተጨማሪ መረጃ ከሰነዱ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እያሳወቅን የደቡብ /ኢ/ክ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት አስተዳደር ቢሮ እንደገና ተሻሽሎ የወጣው የግዢ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 70/2017 እና መመሪያው ላይ የተደረገውን ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ሰርኩላር ተፈጻሚ ይደረጋል።
ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0916 029 511/0913 725 758 መደወል ይችላሉ
አድራሻ፡- ዲላ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት አስተዳደር ቢሮ