ኦላ ኢነርጂ ኢትዮጵያ ሊሚትድ በአዲስ አበባ ከተማ በዋናው መስሪያ ቤት እና በቦሌ አቬየሽን ውስጥ የሚገኘውን ለካፍቴሪያ/ለሬስቶራንት አገልግሎት የሚውል ቦታ ለማስተዳደር ብቁ የሆኑ እና ተሞክሮ ያላቸውን አገልግሎት ሰጪዎች አወዳድሮ ማስገባት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ኦላ ኢነርጂ ኢትዮጵያ ሊሚትድ በአዲስ አበባ ከተማ በዋናው መስሪያ ቤት እና በቦሌ አቬየሽን ውስጥ የሚገኘውን ለካፍቴሪያ/ለሬስቶራንት አገልግሎት የሚውል ቦታ ለማስተዳደር ብቁ የሆኑ እና ተሞክሮ ያላቸውን አገልግሎት ሰጪዎች አወዳድሮ ማስገባት ይፈልጋል


Reporter (Oct 21, 2026)

ለካፌ /ሬስቶራንት ለሚውል ቦታ የወጣ ጨረታ TENDER FOR CAFÉ/RESTAURANT SPACE

ኦላ ኢነርጂ ኢትዮጵያ ሊሚትድ በአዲስ አበባ ከተማ በዋናው መስሪያ ቤት እና በቦሌ አቬየሽን ውስጥ የሚገኘውን ለካፍቴሪያ /ለሬስቶራንት አገልግሎት የሚውል ቦታ ለማስተዳደር ብቁ የሆኑ እና ተሞክሮ ያላቸውን አገልግሎት ሰጪዎች አወዳድሮ ማስገባት ይፈልጋል።

  • ለመወዳደር የሚፈልጉ አመልካቾች

1. በካፍቴሪያ ወይም ሬስቶራንት ከ3(ሶስት) አመት ያላነሰ ልምድ ያላቸው ቢሆን ይመርጣል።

2. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የተረጋገጠ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው

3. ከሚመለከተው የጤና ቢሮ የምግብና መድኃኒት ተቆጣጣሪ ባለስልጣን በዘርፉ የተሰጠ የሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ ፤

4. ከላይ የተጠቀሰው ሥራ የሚጠይቀውን ለመስሪያ ካፒታል ገንዘብ በግላቸው የማቅረብ አቅም ያላቸው ፤

5. ወቅታዊ የሆነና ያለፉትን 6 (ስድስት) ወራት የሚያሳይ በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ስቴትመንት ማቅረብ የሚችሉ ሆነው ከባንኩ የማረጋገጫ ደብዳቤ ማምጣት የሚችሉ ፣

  • ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አመልካቾች

1. የጨረታ ሰነዶቹን ከጥቅምት 11,2019 ዓም እስከ ጥቅምት 20,2019 ዓም በሥራ ሰዓት ኦላ ኢነርጂ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኘው የኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት የእንግዳ መቀበያ በመገኘት የማመልከቻ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

 2. ጨረታው ጥቅምት 20,2019 ዓም ከቀኑ 10:00 ይዘጋል።

3. ከላይ ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ በኋላ የሚቀርብ የማመልከቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።

4. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኦላ ኢነርጂ ኢትዮጵያ ሊሚትድ
ዋናው መስሪያ ቤት የሰው ኃይል አስተዳደር ን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወፈዳ 7 የቤት ቁጥር 280
ስልክ 9990 ወይም 0114170450


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *