2merkato.com (Oct 23, 2026)
የጨረታ መለያ ቁጥር: LSS/ERP/01/2026
የድርጅቱ ስም: ላየን ሴኩሪቲ ሰርቪስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (Lion Security Service PLC)
የጨረታው ርዕስ: ነባሩን የ ERP ሶፍትዌር በአዲስ ዘመናዊ ERP ሲስተም የመቀየር፣ የማበጀት (Customization) እና የመተከል (Deployment) ስራ።
ላየን ሴኩሪቲ ሰርቪስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በዋናነት በደህንነትና ጥበቃ አገልግሎት ዘርፍ የተሰማራ ድርጅት ሲሆን፤ ቀደም ሲል ሲጠቀምበት የነበረውን አሮጌ የERP ሶፍትዌር ሙሉ በሙሉ በአዲስ እና ዘመናዊ የERP ሲስተም ለመቀየር ይፈልጋል።
በመሆኑም በድርጅታችን ዋና መሪያ ቤት የተዘጋጀ የኔትወርክ መሰረተ ልማት (Existing Network Infrastructure) ያለ በመሆኑ፣ አዲሱን የERP ሶፍትዌር አበጅተው፣ ተክለው፣ ነባር ዳታዎችን አሸጋግረው (Data Migration) እና ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ አስገብተው (Deploy አድርገው) ማስረከብ የሚችሉ ብቁ እና ልምድ ያላቸውን የሶፍትዌር አልሚ/አቅራቢ ካምፓኒዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
- የሲስተሙ ዋና ዋና መስፈርቶችና የሥራ ወሰን (Scope of Work): አሸናፊው ካምፓኒ የሚተክለው የERP ሶፍትዌር የጥበቃ ድርጅቶችን ልዩ ባህሪ ያገናዘበ ሆኖ የሚከተሉትን ዋና ዋና ክፍሎች (Modules) ያካተተ መሆን አለበት፦
የሰው ሀብት እና የደመወዝ አስተዳደር (HR & Payroll Module): የብዙ ሰራተኞችን ማህደር፣ የፈረቃ (Shift) ምደባ፣ የክትትል (Attendance) እና የደመወዝ/አበል ስሌትን በጥበቃ አገልግሎት ባህሪ ልክ የሚያቀናጅ።የፋይናንስና አካውንቲንግ (Finance & Accounting Module): ዋና መዘገብ፣ ገቢና ወጪ፣ የባንክ ሂሳብ፣ የታክስ (VAT/Pension/Income Tax) እና የሂሳብ ሪፖርቶችን በራስ-ሰር የሚያወጣ።
የንብረት፣ ግዥና መጋዘን አስተዳደር (Inventory, Procurement & Asset Management): የድርጅቱንና የደንበኞችን ንብረቶች (ዩኒፎርሞች፣ የመገናኛ መሳሪያዎች ወዘተ)፣ የግዥ ፍሰት እና የመጋዘን እንቅስቃሴን የሚያስተዳድር።
የኦፕሬሽንስና ደንበኞች አስተዳደር (Operations & Client Contract Management): የደንበኞችን ኮንትራት፣ የጥበቃ ቦታዎች (Sites) እና የሰራተኞች ስምሪትን በዳሽቦርድ የሚያሳይ።
መረጃ የማሸጋገር ስራ (Data Migration): ከነባሩ የቆየ ሲስተም ላይ አስፈላጊ መረጃዎችን ወደ አዲሱ ሲስተም የማሸጋገር ስራን ያካትታል። - ተጫራች ካምፓኒዎች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ። ድርጅቱ ወይም ካምፓኒው የ ERP ሶፍትዌር የመተከልና የመዘርጋት (ERP Implementation) በቂ ልምድና ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል (በተለይም በሰራተኛ ብዛት ባላቸው የአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ላይ የሰራ ቢሆን ይመረጣል)። ሲስተሙን ከተከለ በኋላ ለስራተኞች ስልጠና (Training) መስጠት እና ከትግበራ በኋላ የቴክኒክ ድጋፍና ጥገና (Post-implementation Support) ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነ።
- የጨረታ ሰነድ አወሳሰድና ማቅረቢያ፡ ተጫራች ካምፓኒዎች የቴክኒክ (Technical Proposals) እና የፋይናንስ (Financial Proposals) ሀሳቦቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ሕዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ቀኑ 11 ሰዓት ድረስ በድርጅታችን ዋና መሥሪያ ቤት በአካል በመቅረብ ማስገባት ይችላሉ።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ ላየን ሴኩሪቲ ሰርቪስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
የቢሮ አድራሻ፡ መገናኛ ከአምቼ ጀርባ ጃፓን መኖሪያ መንደር በሚገኘው ቢሮአችን በአካል መምጣት ይችላሉ፡፡
ስልክ ቁጥር፡ 0930 51 92 02/0922 46 40 44 ኢሜይል፡ lionsecurity.tender@gmail.com
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ