Addis Zemen (Oct 24, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብ/ክ/መ በደቡብ ምእራብ ኦሮሚያ ዞን የነዲ ጊቤ ወረዳ መንገዶች እና ሎጅስቲክ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ በ2019 ዓ.ም ለሚያከናውነው የተለያዩ መንገዶች ግንባታና ጥገና ማሽነሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ አመልካቾች በሙሉ የወረዳው መንገዶችና ሎጅስቲክ ጽ/ቤት በሚያወጣው የጨረታ መስፈርት እና ደንብ መሰረት መጥታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የማሽነሪዎቹ አይነት
- ዶዘር CAT D8R
- ግሬደር SANY STG-230
- ኤክስካቫተር CAT 330 DL, CL
- ሮለር 16 Ton
- ሎደር
- Shower Truck 16m3
- ገልባጭ 14 m3
ሲሆኑ አመልካቾች፡-
1. ህጋዊ የማሽን ማከራየት ፍቃድ ያላቸው።
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢና ቲን ቁጥር ያላቸው።
3. የ2019 ዓ.ም የመንግስት ግብር የከፈሉና የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ።
4. የማሽነሪዎቹ ሞዴል 2016 G.C እና ከዚያ በሁዋላ መሆን አለበት።
5. ከዚ በፊት በሰሩበት የመልካም አፈጻጸም ምስክር ወረቀት ያላቸው።
6. የማሽነሪዎቹን ማስጫኛና ተያያዥ ወጪዎች በራሳቸው መሸፈን የሚችሉ ሆኖ በሚያቀርቡት የማሽነሪዎች ዋጋ ውስጥ ታሳቢ ማድረግ ይኖርባችዋል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት በወረዳው ገቢዎች ባለስልጣን ቀርበው የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) 500,000 በባንክ በተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይኖርባችዋል።
9. ተጫራቾች የቅድመ ማጣሪያ ቴክኒካል ዶክመንት በጥንቃቄ በመሙላት እና አስፈላጊ ዶክምንቶችን በማያያዝ ኦርጅናል፣ ፎቶ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ (CPO) ለየብቻ በማሸግ ተገቢውን መረጃ በፖስታዎቹ ላይ በጉልህ በመጻፍ ሶስቱንም በሌላ ኤንቨሎፕ ማሸግ እና ቴክኒካል ዶክመንት በማለት መጻፍ ይኖርባቸዋል።
10. የዋጋ ማቅረቢያ (ፋይናንሻል) ዶክመንት ኦርጂናል እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ተገቢውን መረጃ በፖስታዎቹ ላይ በጉልህ በመጻፍ ሁለቱንም በሌላ ኤንቨሎፕ በማድረግ ተገቢውን መረጃ በፖስታዎቹ ላይ በመጻፍ ሁለቱንም በሌላ ኤንቨሎፕ በማሽግ፤ በመጨረሻም ቴክኒካል እና ፋይናንሻል አንድ ላይ በሌላ ኤንቨሎፕ በማሸግ አስፈላጊውን መረጃ በጉልህና ግልጽ በሆነ ጽሁፍ በመጻፍ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ 16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
11. ጨረታው በ16 ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ6፡30 ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት ውስጥ በይፋ ይከፈታል።
12. ስርዝ ድልዝ ያለባቸውንና በግልጽ የማይነበቡ አሻሚ ፊደሎች ያላቸው አንዲሁም የማይነበቡ ሰነዶች ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የላቸውም።
ማሳሰቢያ፡- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጮችን ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ደቡብ ምእራብ ኦሮሚያ ዞን ነዲ ጊቤ ወረዳ ዲምቱ ከተማ
ለተጨማሪ መረጃ :- 09 24 43 75 59 አልያም በወረዳው መንገዶች ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በኦሮሚያ ብ / ክ / መ በደቡብ ምእራብ ኦሮሚያ ዞን የነዲ ጊቤ ወረዳ መንገዶች እና ሎጅስቲክ ጽ/ቤት