በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ/ዞን/ የእንሳሮ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2019 በጀት አመት የተለያዩ እቃዎችን ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ/ዞን/ የእንሳሮ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2019 በጀት አመት የተለያዩ እቃዎችን ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 24, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር/ 51/2019ዓ.ም

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ/ዞን/ የእንሳሮ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2019 በጀት አመት ከመደበኛ በጀት ላይ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችን ለመግዛትና ለማሰራት ስለሚፈልግ በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መመዘኛዎችን የሚያሟሉና በዘርፍ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ዘዴ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም

  • ሎት1 የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች የኮምፒውተር ቀለሞች እና የአላቂነት ባህሪ ያላቸው እቃዎች
  • ሎት2 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • ሎት3 ቋሚ እቃዎች /ፈርኒቸር/
  • ሎት4 የጽዳት እቃዎች
  • ሎት5 የህትመት ስራዎች
  • ሎት6 የተዘጋጁ ልብሶች/ብትንጨርቅ/ጫማዎች
  • ሎት7 ቋሚ እቃዎች ጥገና
  • ሎት8 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገናዎች

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋያ መለያ ቁጥር/tin/ያላቸው፡፡

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. ተጫራቾች ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ1-2 የተጠቀሱትንና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

4. በማንኛውም ግዥ ለእቃዎች ከብር 20000/ሀያ ሽህ/ በላይ እና ለአገልግሎት ከብር 10000/አስር ሽህ/ በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈጸምለት ክፍያ ላይ 3% የቅድመ ግብር/with hold/ ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡

5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ከግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን/የስ/ሂደት ቢ.ቁ 03 በመቅረብ ዘውትር በስራ ሰአት መውሰድ ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የሚቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መስሪያ ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡

7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃዎችን የሚዘገጁበት ቋንቋ አማርኛ መሆን አለበት፡፡

8. መ/ቤቱ የእቃዎችን ናሙና የሚፈልጉ ከሆነ ተጫራቾች የጠየቁትን ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡ ጨረታው የሚለየው በጥቅል ዋጋ ነው፡፡

10. በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡

11. ተጫራቾ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ የእቃ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በአቢሲኒያ ባንክ ብቻ በሲፒኦ/በጥሬ ገንዘብ/ በጽ/ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስያዝ አለባቸው፡፡

12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ዋና ኦርጅናል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ስም፤ ፊርማና ሙሉ አድራሻ በመፃፍ እ/ወ/ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰአት ተዘግቶ በዚያው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ5፡00 ሰአት በግልጽ ይከፈታል፡፡

13. በማንኛውም ሁኔታ ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ወይም ተመስርቶ መጫረት አይችልም፡፡

14. ግዝ ፈፃሚው አካል ውል ከመግባቱ በፊት ከአሸናፊው ተጫራች የቀረበውን ዋጋ ሳይቀይር እስከ 20% ለመቀነስ ወይም መጨመር እንደሚችል ማወቅ አለባቸው፡፡

15. የጨረታው መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡ አሸናፊ የሆነ ድርጅት በግዥ ፈጻሚ መስሪያ ቤት አቅራቢያ በሚገኝ ዐ/ህግ ጽ/ቤት በመቅረብ 10% ውል በመግባት ለግዥ ፈጻሚ መስሪያ ቤት ንብረት ክፍል ማስረክብ አለባቸው፡፡

16. ጨረታ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፤ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ይሆናል፡፡

17. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ብሄራዊ በአላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡

18. የመስሪያ ቤቱ መገኛ ከዞኑ ደ/ብርሀን ከተማ 86 ኪ.ሜትር ከአዲስ አበባ ደግሞ 130 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡

19. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912 841 935 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሽዋ/ዞ ን / የእንሳሮ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡ