Addis Zemen (Oct 25, 2026)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 17/2019
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየገነባቸው ላሉት
1. ለእንጅባራ ትራፊክ ኮምፕሌክስ ፕሮጀክት፣ ለጋሸና ብልባላ ላሊበላ መንገድ ስራ ፕሮጀክት እና ለጋሽና ኮን–ጨጎማ መንገድ ስራ ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውል 60/70 bitumon ፣ primo coat (MC-30) እና Tack coat (RC-70) አቅርቦት በጨረታ ቁጥር 17/2019 ግዥ ለመፈጸም ህጋዊና ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፡–
1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፤
2. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 1.5% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፤
3. የጨረታ ሰነዱን ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ባ/ዳር ከተማ (አፄ ቴወድሮስ ክ/ከተማ ቀበሌ 11) አባይ ራስ ቀበሌ እና አ/አበባ ለገሃር አመልድ ህንፃ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ 7ኛ ፎቅ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 / ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፤
4. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለጨረታ ቁጥር 17/2019 እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ባህር ዳር ዋናው ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ ለጨረታ ቁጥር 17/2019 በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል። የተጠቀሱት የመክፈቻ እና የመዝጊያ ቀናቶች የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በእለቱ ቀን 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፤
5. የጨረታው ውድድሩ በሎት/በምድብ/ ድምር ዋጋ የሚታይ ሲሆን በአንድ ሎት /ምድብ/ ለተጠየቁ የስራ ዝርዝሮች ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሞላት አለበት፤
6. በጨረታ የተሞላው ዋጋ የጨረታ ሠነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ45 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፤
7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፤
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር :-
ባህር ዳር፡– 058-218-0538 / 09-18-01-06-17 / 09-21-26-13-00
አዲስ አበባ፡– 011 126 5338 / 09-18-80-03-64 / 09-20-24-93-20
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን