በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ለ3B+G+11 ቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ እና ለB+G+7 ሰንበት ት/ቤት ሕንፃ ፕሮጀክቶች መዋቅራዊ ፍሬም ግንባታ የንድፍ ክለሳ፣ የግንባታ ቁጥጥር እና የውል አስተዳደር የማማከር አገልግሎት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ለ3B+G+11 ቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ እና ለB+G+7 ሰንበት ት/ቤት ሕንፃ ፕሮጀክቶች መዋቅራዊ ፍሬም ግንባታ የንድፍ ክለሳ፣ የግንባታ ቁጥጥር እና የውል አስተዳደር የማማከር አገልግሎት ይፈልጋል


Reporter (Oct 25, 2026)

ግልፅ ጨረታ

በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ለ3B+G+11 ቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ እና ለB+G+7 ሰንበት ት/ቤት ሕንፃ ፕሮጀክቶች መዋቅራዊ ፍሬም ግንባታ የንድፍ ክለሳ፤ የግንባታ ቁጥጥር እና የውል አስተዳደር የማማከር አገልግሎት የወጣ ግልፅ ጨረታ

(የማማከር ሥራ – አማካሪ መምረጥ)

ሀገር፡ ኢትዮጵያ

የፕሮጀክቱ ስም: – 3B+G+11 ቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ እና B+G+7 ሰንበት ት/ቤት ሕንፃ ግንባታ

መስፈርቶች፡–

  1. የደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን የ3B+G+11 ቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ እና የB+G+7 ሰንበት ት/ቤት ሕንፃ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ደረጃ-1 አማካሪ ድርጅት አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።
  2. የጨረታው ማስታወቂያ ጋዜጣ ላይ ከወጣ ጀምሮ ለተከታታይ 13 የቀን መቁጠሪያ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታው ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን በ13ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሲሆን በዛኑ ዕለት 4:30 ይከፈታል።
  3. ተጫራቾች የግንባታ ሳይቱን እንዲጎበኙ እና ቅድመ ጨረታ ውይይት እንዲያደርጉ ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ/ም ካቴድራሉ ከጠዋቱ 4፡00 ጨረታውን ከገዙ ተጫራቾች ጋር ስብሰባ የሚያካሄድ ይሆናል።
  4. የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 መሣለሚያ የሚገኘው ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያን ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከጠዋቱ 2፡00 – 6፡00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ 7፡00 – 11፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 2,000 (ሁለት ሺ ብር) በመክፈል በአካል ቀርቦ መውሰድ ይቻላል። በተጨማሪም በኢሜል amchatederalimat@gmail.com  ወይም በቴሌግራም DGKamanuel28 (0921876472) የማይመለስ ብር 2,000 (ሁለት ሺ ብር) በካቴድራሉ ልማት ስም በተከፈተው የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000215809238 በማስገባት የተከፈለበትን ስሊፕ በቴሌግራም በማያያዝ በሶፍት ኮፒ ሰነዶቹን መውሰድ ይችላሉ።

5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፦

  • የ 2018 ዓ.ም በተቋቋመው ሀገር ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ወይም የንግድ ድርጅት የምዝገባ ሰርተፍኬት
  • ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ለ 2018 ዓ.ም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት
  • ተጫራቾች የT &VAI ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት ሊኖራቸው ይገባል።
  • ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የግብር ክሊራንስ ሰርተፍኬት ሊኖራቸው ይገባል።
  • በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የመንግስት ግዢ እና ንብረት ባለሥልጣን ዝርዝር የምዝገባ ሰርተፍኬት
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ኦርጅናል ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በተለየ ኤንቨሎፕ በባንክ በተረጋገጠ በካቴድራል ስም ማስያዝ አለባቸው።
  • ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሱት ተመሳሳይ ፕሮጀክት ሥራዎች ላይ ልምድ ያላቸው መሆን አለባቸው።

አድራሻ፡–

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 መሣለሚያ አካባቢ ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን፤ የካቴድራሉ አስተዳደር ሕንፃ ግራውንድ ወለል።

ስልክ ቁጥር:- 011-276-3709/ 09 27-28-42-92/ 09 21-87-64-72

የፖስታ ሳጥን 14206፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ካቴድራሉ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን

 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *