Reporter (Oct 25, 2026)
የጨረታ ቀን ማራዘምን ይመለከታል
Ref. No.NC/PUR/62/26
ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውል VFD ABB ACS550-01-125A-4 በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ጨረታ ማውጣቱ ይታወሳል።
በመሆኑም ተጫራቾች
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 3 ወራት ህጋዊ ሆኖ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. 100,000.00 (መቶ ሺህ) ብር ማስያዝ አለባቸው።
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ያለምንም ክፍያ አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ በሚገኘው ቢሮአች ከታች በተጠቀሱት አድራሻ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከላይ የተገለጸውን VFD ABB ACS550-01-125A-4 ጠቅላላ ዋጋ ከቫት በፊት በመሙላት በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 10 የስራ ቀናት አዲስ አበባ ጦር ሀይሎች አዋሽ ወይን አካባቢ ኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ ህንጻ ስልክ፡ 251-11 442 1928/09 34-64-64- 77/09 60-36-71-36 ግዢ ክፍል እና ድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ስልክ ቁጥር 09 35-40-49-76/09 30-28-34-90/09 35-98-50- 83 ግዢ ክፍል በታሸገ ፖስታ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው ጥቅምት 25/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ ጥቅምት 30/2019 ዓ.ም ድሬዳዋ በሚገኘው ናሽናል ሲሚንቶ ኢማ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች የጥገናውን ሁኔታ/ሥራ/ በድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር ቅጥር ግቢ ውስጥ ተገኝተው መመልከት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡–
- ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጥበታል። መ/ቤቱም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
ድርጅቱ!
ከዚህ በፊት የወጣውን ጨረታ ለመመልከት እባክዎን ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
https://tender.2merkato.com/tenders/6aba5dcd0a538aabb8000001