የካፋ ዞን ፋይናንስና መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞን ማዕከል ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የካፋ ዞን ፋይናንስና መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞን ማዕከል ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 28, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ / ግ/ጨ/ቁጥር 04/2017

የካፋ ዞን ፋይናንስና መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞን ማዕከል ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾች በመጋበዝ እንደሚከተለው በሎት በመከፋፈል እስከ በጀት ዓመቱ ማብቂያ ማለትም እስከ ሰኔ 30/2019 ዓ.ም ድረስ፦

ሎት .1. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ሎት .2. በካፋ ዞን ግብርና መምሪያ በጊምቦ ወረዳ ህብረት ቀበሌ ቡቄ –ኮሾ ዘርፈ–ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኝ ጣቢያ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ግብዓቶች ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡–

ስለዚህ ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ

1. ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ፣ ከገቢዎች ባለስልጣን የተሰጠ ክሊራንስ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ፣ የቫት ፣ የቲን ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ዶከመንት ሊገዙ ሲመጡ ኦርጅናሉን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡

3. በመሆኑም ተጫራቾች ለሁሉም ሎቶች ለእያንዳንዳቸዉ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 / አምስት መቶ ብር/ ካፋ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ቀርበው በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ለተከታታይ 15 ቀናት ካፋ ዞን ፋይናንስ መመሪያ ግዥ ንብ/አስ/ሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ ፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO (Certified payment order) ፣በጥሬ ገንዘብ እና በቼክ በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ስም በማሰራት ከኦሪጅናል ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ ግዴታ አለባቸዉ፡፡ ስለዚህ ለሎት .1. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 100,000.00 / አንድ መቶ ሺህ ብር/ እና ለሎት .2. ሎት በካፋ ዞን ግብርና መምሪያ በጊምቦ ወረዳ ህብረት ቀበሌ ቡቄ –ኮሾ ችግኝ ጣቢያ አገልግሎት የሚውል የተለያዮ ግብዓቶች ግዥ 80,000.00 / ሰማኒያ ሺህ ብር/ ኦርጅናል ፋይናንሻል ሠነድ ጋር በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ ስም በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በመሆኑም ቴክኒካል ዶክመንት የሚያስፈልገው ለሎት -1- ብቻ ነው፡፡

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሠነዱ ላይ በመጻፍ በሰም/በሙጫ/ በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ በመቅረብ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

6. የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡በመከፈቻዉ ዕለት የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም:: 15 ተከታታይ ቀናት የተባለው ቅዳሜና እሁድ ጨምሮ የሚቆጠር ነው::የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ያለመገኘት የጨረታውን የመከፈት ሂደት አያስተጓጉልም፡፡

7. ተጫራቾች ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የዉል ማስከበሪያ /performance bond/ ለማስያዝ ፈቃደኛ መሆን አለባቸዉ፡፡ አሸናፊዉ ድርጅት ከላይ ሎት -1- እና ለሎት .2. የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በሙሉ በራሱ ወጪ ካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አቅርቦ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡ ተጫራቾች አሰሪዉ መ/ቤት ያዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያ /የቴክኒካል/ ዶክመንት መጠይቅ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል::

8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 331 1826 በመደወል መጠየቅ ይቻላል!!

የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

ቦንጋ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *