በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የቀላል መኪና መለዋወጫ እቃዎች (ሎት 1) እና የቀላል መኪና ተሽከርካሪ ጎማ (ሎት 2) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የቀላል መኪና መለዋወጫ እቃዎች (ሎት 1) እና የቀላል መኪና ተሽከርካሪ ጎማ (ሎት 2) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 31, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደ/ወ/ዞን የወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት1 በተደጋጋሚ የሚቀየሩ የቀላል መኪና መለዋወጫ እቃዎች እና
  • ሎት 2.የቀላል መኪና ተሽከርካሪ ጎማ በመደበኛ በጀት በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በራስ ሀይል የግዥ ስልት አወዳድሮ በሎት ድምር ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. ጨረታውን ይፋ ያደረገው የወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ነው የተሟላ አድራሻውም በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ ቢስቲማ ከተማ ከደሴ 47 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ቦታ

2. የሚወዳደሩበትን እቃዎች በተመለከተ በየሎቱ ሲሆኑ ርክክብ የሚፈጸምበት ቦታ ወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በአራቱም ንብረት ክፍል ይሆናል፡፡

3. የግዥ ዘዴው ግልጽ ጨረታ ሲሆን የጨረታ መለያ ቁጥሩ መደበኛ 001/2019 ነው፡፡ 

4. በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ እጩ ተወዳዳሪዎች ሊያሟሉ የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/ ፣ በዘርፉ የተገለጸ የንግድ ስራ ፍቃድ እና ምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ፣ የግዥው መጠን ከብር 500,000.00/አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ 

5. የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት ብር 300/ሶስት መቶ/ ወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡

6. የመጫረቻ ሰነዱን ማሰታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ21/02/2019 ጀምሮ እስከ 1/03/2019 4፡00 ሰዓት ድረስ ከወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 መውሰድ ይቻላል፡፡

7. የመጫረቻ ሰነዱ የመጨረሻ ማስረከቢያ ቀን 1/03/2019 እና የሚከፈትበት ቀን- 1/03/2019 ሰአት 4፡30 ይሆናል፡፡

8. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በጨረታው አከፋፈት ላይ መገኘት የሚችሉ መሆኑን፤

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ና በተጫራች መመሪያ ላይ በተገለጹት መሰረት ብር 71,385/ሰባ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሰማኒያ አምስት ብር/ ለመኪና እቃ ፋስት ሙቪንግ እና ብር 30,030 /ሰላሳ ሺህ ሰላሳ ብር/ ለመኪና ጎማ ማስያዝ አለባቸው፡፡

10ለእቃ ከ20,000 በላይ ግዥ ሲፈጸም 3 ፐርሰንት ለአቅራቢው ከሚፈጸምለት ክፍያ ላይ ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር መሆኑ

11. የመንግስት መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብት ያለው ሲሆን በዚህም ምክንያት ተጫራቹ ላወጣው ወጭ መስሪያ ቤቱ ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን

12.ተጫራቾች በጨረታውለመሳተፍ ከተራቁጥር 1-11 የተጠቀሱትንመረዳትና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ የሚቀርበው ፎቶ ኮፒ የሚነበብ መሆን አለበት፡፡

13.የሚገዙት የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ(ስፔስፊኬሽን) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡

14. ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡- 033 221 0025 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ
ንብረት አስተዳደር ቡድን 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *