የቦታ ስፋት 152 ካ.ሜ. የሆነ ቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የቦታ ስፋት 152 ካ.ሜ. የሆነ ቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Nov 01, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ሄኖክ ንጋቱ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ብርቄ ወ/መድህን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/325844 በ01/05/2016ዓ/ም እና በኮ/ መ/ቁ/330784 በ26/06/2016ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ በቀድሞ ወረዳ 04 በአሁኑ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 173 የሆነ መኖሪያ ቤት የይዞታ መለያ ቁጥር AA000030400359 የተመዘገበ ካርታ ያለው የቦታ ስፋት 152 ካ.ሜ. ይዞታው በሰሜን 6 ሜትር ስፋት የውስጥ ለውስጥ መንገድ የሚያዋስነው ሲሆን መንገዱ ተግባራዊ ሲደረግ 28.23 ካ/ሜ ስፋት ያለው ቦታ የሚቀነስ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 8,273,896 ( ስምንት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰባ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ስድስት) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 23 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍር ድ
አፈፃፀም ጽ / ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *