Addis Zemen (Nov 01, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስፋ / ግጨ/046/2019
በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ (አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ) ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የጥበቃ ሠራተኞች ጫማ እና የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የጥበቃ ሠራተኞች የስራ ጫማ(Leather shoe long boots)
- ሎት 2 ፡የጥበቃ ሠራተኞች የስራ የደንብ ልብስ( Trawuhers and shirt)
ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላችሁ አካላት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀናት ድረስ ለግሀር አሮጌ ባቡር ጣቢያ ወደ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን 4ኛ ክፍለ ጦር አካባቢ የሚገኘው አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ በማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቀርበው ለዚህ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
1. ቫት ተመዝጋቢ የሆነና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin.No) ያላቸው በሚወዳደሩበት ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በመንግስት መ/ቤት ግዢ ለመወዳደር እንደሚችሉ ከገቢ ሰብሳቢ ድርጅቶች ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች በጨረታ መመሪያው ላይ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ለእያንዳንዱ ሎት 5000 (አምስት ሺህ ብር) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ማቅረብ የሚችሉ።
3. የሚጫረቱበትን ዋጋ በእያንዳንዱ በጨረታ ሰነድ መሠረት እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል።
4. ጨረታው በሁለት የታሸገ ፖስታ መቅረብ ያለበት ሲሆን በቴክኒካል ፖስታ አስፈላጊ ሰነዶች ትክክለኛ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ አብሮ መቅረብ አለበት።
5. ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል
6. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ሊገኙ ፈቃደኛ በሆኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት ይከፈታል።
7. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ነገሮች ማሻሻል ወይም መተው አይችልም።
8. የጨረታው ተሳታፊዎች አቅራቢዎች ከዚህ በላይ የተገለጹትን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለፋብሪካው ገቢ ሆኖ ተጫራቹ ከጨረታው ይሰረዛል።
9. ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ ለገሀር አሮጌ ባቡር ጣቢያ ወደ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን 4ኛ ከፍለ ጦር አካባቢ የሚገኘው አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ በማስተባበሪያ ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 09-13-99-43-49 ወይም 09-73-42-13-43 በመደወል ወይም ዘወትር በስራ ሰዓት በግንባር በመቅረብ ማነጋገር ይችላሉ።
10. ማስረከቢያ ቦታ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ። ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ