በአብክመ የኦሮሞ ብ/ዞን የደ/ጨ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የመንገድ ጥገና እና አዲስ መንገድ ቆረጣ ሥራ የሚሆኑ የተለያዩ ማሽነሪዎች (ዶዘር፣ ግሬደር፣ ሎደር፣ ሮለር፣ የውሃ ቦቲ እና ገልባጭ መኪና) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት/ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአብክመ የኦሮሞ ብ/ዞን የደ/ጨ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የመንገድ ጥገና እና አዲስ መንገድ ቆረጣ ሥራ የሚሆኑ የተለያዩ ማሽነሪዎች (ዶዘር፣ ግሬደር፣ ሎደር፣ ሮለር፣ የውሃ ቦቲ እና ገልባጭ መኪና) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት/ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 02, 2026)

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ የኦሮሞ ብ/ዞን የደ/ጨ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ስር የሚገኘው መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ከቀራሮ ቀብር-ዲንዲን ዶዶ እና ሜጢ ሰርጤ ለሚሰራው የመንገድ ጥገና ዲንዲን-ቢላቻ ሙዲ ሸክላ የሚሰራ አዲስ መንገድ ቆረጣ ስራ የሚሆን የተለያዩ ማሽነሪዎች ማለትም

  • ዶዘር፤ ግሬደር፤ ሎደር፤ ሮሎ የውሃ ቦቲ እና ገልባጭ መኪና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በአሸናፊው ለማሰራት /ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን መስፈርቶቹም፡-

  1. በዘርፋ ህጋዊ 2019 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ንግድ ምዝገባ፤ የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. ሊብሬ ማቅረብ የሚችል፤
  3. ተጫራቾች የምዝገባ የምስክር ወረቀት (Tin No) አብረው ማያያዝ የሚችሉና ከ500,000 ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የያዘ ከኦሮ/ብ/ዞ/ደ/ጨ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ለ10/አስር/ ተከታታይ ቀናት ገዝተው በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ /ኢንቨሎፕ/ በማሸግ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ቀን 4፡10 የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን ሆኖም የመክፈቻው ዕለት በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች ለሞሉት ለጠቅላላ የጨረታ መጠን ላይ ብር 100,000 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት መረጃ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለበለጠ መረጃ የተጫራቾች መመሪያ ላይ መረዳት ይቻላል ወይም በስልክ ቁ.0335540225/0294 መደወልና መጠየቅ ይችላሉ፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በአብክመ የኦሮሞ ብ/ዞን

የደ/ጨ/ ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *