የሰንዳፋ በኬ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ3 ሎቶች የተከፈሉ ዕቃዎችን (Lot 1: አላቂ የጽህፈት ዕቃዎች/Stationary፣ Lot 2: HDPE fitting & GS fitting፣ Lot 3: የደንብ ልብስ/Uniform) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሰንዳፋ በኬ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ3 ሎቶች የተከፈሉ ዕቃዎችን (Lot 1: አላቂ የጽህፈት ዕቃዎች/Stationary፣ Lot 2: HDPE fitting & GS fitting፣ Lot 3: የደንብ ልብስ/Uniform) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 02, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የሰንዳፋ በኬ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዘት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት

  • Lot.1. አላቂ ዕቃ (Stationary)
  • Lot.2. HDPE fitting & GS fitting
  • Lot .3. (የደንብ ልብስ uniform ናቸው፡፡

ስለዚህ

1. በተጠቀሱት የንግድ ዘርፎች ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያለውና 2018 ዓ.ም ግብር የከፈለ፡፡

2.የአቅረቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፡፡

3. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነና በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በሰንዳፋ በኬ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ 4 ቁጥር በመምጣት የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር ብቻ) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡

5.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ CPO (bid bond) 2% በሲንቄ እና ኦሮሚያ ባንክ ማስያዝ ይኖርበቸዋል፡፡

6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሠነዱን በመግዛት ዋጋ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ በሰንዳፋ በኬ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 3 ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በ11ኛ ቀን ከሰዓት 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 ይከፈታል፡፡

7.የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀናት ቅዳሜና ዕሁድ በዓላት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡

8 .መ/ቤቱ የተሻላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡

ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከፈለገ በስልክ ቁጥር 0116860068 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሰንዳፋ በኬ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *