Addis Zemen (Nov 02, 2026)
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ገላን ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ የደንብ ልብስ ፣ የእስቴሽነሪ እቃዎች፣ የህክምና መሳሪያዎች፣ አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ እንዲሁም ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ቧንቧና ኤሌክትሪክ እቃዎች፣የህትመት ውጤቶች ጨምሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለፈለገ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታ እድትሳተፉ ይጋብዛል።
|
ተ.ቁ |
የሎት ዝርዝር |
የሲፒኦ መጠን |
|
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ |
30,000 |
|
ሎት 2 |
አላቂ የስቴሽነሪ እቃዎች |
20,000 |
|
ሎት 3 |
የቧንቧ ና ኤሌክትሪክ እቃዎች |
8,000 |
|
ሎት 4 |
አላቂ የጽዳት እቃዎች |
30,000 |
|
ሎት 5 |
ቋሚ የቢሮ እቃዎች |
40,000 |
|
ሎት 6 |
የተለያዩ የህትመት ውጤቶች |
20,000 |
|
ሎት 7 |
መድሃኒትና የህክምና መሳሪያዎች |
70,000 |
በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ፡–
1. የዘመኑ የታደሰ ፍቃድ ያላቸው፣ በመንግስት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት።
2. በተጨማሪ አሴት ታስክ ተመዝጋቢነት መረጃ ማቅረብ አለበት።
3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በሎቱ ፍለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የገላን ጤና ጣቢያ ስም በባንከ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ለእያንዳንዱ ለሚሳተፉበት ሎት ማስያዝ ግዴታ አለበት።
4. የጨረታ ጊዜ ጸንቶ የሚቆየው ለ45 ቀን ብቻ ነው።
5. ተጫራቾች ዘወት በስራ ሰዓት በጤና ጣቢያው የፋይናስ ቢሮ ቁጥር 56 የጨታ ሰነዱ በየሎቱ የማይመለስ 300 ብር በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ።
6. በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ተጫራቾች በአገር ውስጥ ምርት ላይ የተሳተፉና መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ብቻ ከክፍያ ነፃ ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ በማጻፍና መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ከዚያ ውጭ ከሆነ ግን (እቃ) እንደማንኛውም ተጫራች ሰነዱን በመግዛትና በየሎቱ የተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ ጨረታውን መሳተፍ ይችላሉ።
7. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች እቃውን በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ መስሪያቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማስገባትና ማስረከብ አለበት።
8. ተጨራቾች የሚያስገቡትን የእቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
9. ተጫራቾች ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዶችን ዋናውንና ፎቶኮፒውን ከማስረጃው ጋር በማደራጀት በታሸገ ፖስታ ጤና ጣቢያው ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው እለት ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሂሳብ ክፍል ይከፈታል፤ ነገር ግን በዘ ቀን በዓል ወይም እረፍት ከሆነ በሚቀጥለው ቀን የሚከፈት ይሆናል።
11. ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
12. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ እደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ ዋስት ማስያዝ ግዴታ አለባቸው።
13. ተጫራቾች ባሸነፉበት እቃዎች ብዛት መስሪያ ቤቱ 20% በመጨመርም 20% በመቀነስም ውል መስጠት ይችላል፤ እንዲሁም ጤና ጣቢያው የተሸለ አማራጮችን ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የታል ዝቅ ብሎ ወደ አዳማ በሚወስደው መንገድ ላይ በሰላም ህንፃ ገላን ሳይት ኮንደምንየም በሚወስደው መንገድ 3000 ሜ ገባ ብሎ ይገኛል።
ስልክ ቁጥር 011-4-35-90-40
አቃቂ ቃሊቲ ክ/ክተማ ወረዳ 12 ገላን ጤና ጣቢያ