በምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የቡሬ ከተ/አስተዳደር ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለቡሬ ከተ/አስ/ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የቡሬ ከተ/አስተዳደር ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለቡሬ ከተ/አስ/ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Nov 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የቡሬ ከተ/አስተዳደር ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለቡሬ ከተ/አስ/ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን ማለትም፡- ሎት 1. የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2. የጫማ ግዥ፣ ሎት 3. የተዘጋጁ ልብሶች እንዲሁም ሎት 4 ብትን ጨርቅ ህጋዊ አቅራቢዎችን በመጋበዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡

3. የግዥው መጠን ከብር 20,000 (ሀያ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ 3 በመቶ ቅድመ ግብር የሚቀነስ መሆኑን እና ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ ላይ የነጠላም ሆነ የጠቅላላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጨረታ ውጭ ይደረጋል፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች በጨረታ መክፈቻ ወቅት ከቀረበው የንባብ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር ልዩነቱ ወደ ላይም ሆነ ወደ ታች ከ3 በመቶ ከበለጠ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡ ተጫራቾች የእያንዳንዱን የነጠላ ዋጋ በእቃው ዓይነት ተባዝቶ ጠቅላላ ዋጋውንም ማስቀመጥ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. የሚገዙ የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አ ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋውን በእያንዳንዱ ሎት 1. ብር 5,500 (አምስት ሽህ አምስት መቶ ብር) ሎት 2. ብር 3,000 (ሶስት ሽህ ብር) ሎት 3. ብር 2,500 (ሁለት ሽህ አምስት መቶ ብር)፣ ሎት 4. ብር 2,000 (ሁለት ሽህ ብር) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌትር አፍ ክሬዲት እና ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ የክፍያ ማዛዣ ማስያዝ አለባቸው፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቡሬ ከተ/አስ/ገ/ል/ጽ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡሬ ከተ/አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡15 ይከፈታል፡፡ እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም  በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን  4፡15 ይከፈታል፡፡

11. አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ድምር ሲሆን በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌትር ኦፍ ክሬዲት እና ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ማስያዝ የሚችሉ እና እቃዎችን ቡሬ ከተ/አስተዳደር ንብረት ክፍል ድረስ የማጓጓዣ ወጭ ችሎ ማስረከብ አለባቸው፡፡

12. ሁሉም እቃዎች በዕቃ ጥራት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ እና በባለሙያ ከተረጋገጠ በኋላ ክፍያ የሚፈጸም መሆኑ አቅራቢው ሙሉ እምነት ያለው መሆን አለበት፡፡

13. መ/ቤቱ ከአሸናፊው ተጫራች ከእያንዳንዱ የአቅርቦት ዓይነት ከውል በፊት 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

15. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 774 11 00 /111 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቡሬ ከ/አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *