Be'kur (Nov 02, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የሽንዲ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት በሽንዲ ከተማ አስተዳደር ሥር ያሉ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ እቃዎችን ማለትም፡- ሎት 1. የጽ/መሳሪያዎች፣ ሎት 2. የፕሪንተር ቀለሞች፣ ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እና ሎት 4. የተዘጋጁ የፈርኒቸር እቃዎችን በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ ግዥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) የምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸዉ፡፡
3. በግብር ዘመኑ ግብር ከፍለዉ ያጠናቀቁ መሆናቸዉን የሚገልጽ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. የግዥዉ መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አብረዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 20 ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ሰዓት በመምጣት ማግኘት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1. ብር 12,000 (አስራ ሁለት ሺህ ብር)፣ ለሎት 2. ብር 3,500 (ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር)፣ ለሎት 3. ብር 17,000 (አስራ ሰባት ሺህ ብር) እና ለሎት 4. ብር 2,000 (ሁለት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸዉ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
8. ተጫራቾች የግዥዉን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
9. ማንኛዉም ተጫራች የዋጋ መሙያዉን በጥንቃቄ በመሙላት በሞሉት ዋጋ ላይ የድርጅታቸዉን ስም፣ ፊርማና ማህተም በማድረግና በማሸግ በፖስታዉ ላይ የመ/ቤቱን እና የአቅራቢዉን ድርጅት ስም እና አድራሻ በመፃፍ በሽንዲ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ጨረታዉ በጋዜጣ በወጣ ቀናቶች ዘወትር በስራ ሰዓት በተዘጋጀዉ ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ፡፡
10. ይህ ጨረታ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ10 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 የሚቆይ ሲሆን ጨረታዉ በ11ኛዉ ቀን ከረፋዱ በ4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በዚሁ ቀን ሎት 1. ከረፋዱ 4፡30 ሎት 2. ከረፋዱ 5፡00፣ ሎት 3. 5፡30፣ ሎት 4. በ6፡00 ጨረታዉ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታዉን ከመክፈት የማያግደን ከመሆኑም በተጨማሪ ለሚወሰኑ ዉሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡ የጨረታዉ መክፈቻ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
11. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ሽንዲ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 449 08 22 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
12. ተጫራቾች እያንዳነዱን ዋጋ ሲሞሉ ግልጽና ተነባቢ መሆን አለበት፡፡ በነጠላም ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ የሆነ ዋጋ ካለ ተጫራቹ ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
13. ተጫራቾች ነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ እንዲሁም ጠቅላላ ዋጋ ድምር በሙሉ መሙላት አለባቸዉ፡፡ አሸናፊ የሚለየዉ በሎት ጠቅላላ ዋጋ ድምር ስለሆነ ነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ እንዲሁም ጠቅላላ ዋጋ ድምር በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
15. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸዉን እቃዎች ሽንዲ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በራሳቸዉ ትራንስፖርት አጓጉዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
16. ግዥ ፈፃሚ መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀዉ የእቃ ብዛት ላይ የዋጋ ለውጥ ሳያደርግ እስከ 20 በመቶ ድረስ ቀንሶ ወይም ጨምሮ ዉል መያዝ (መግዛት) ይችላል፡
የሽንዲ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት