አጉንታ ተገጣጣሚ ቤቶች ኃ/የተ/የግ/ ማህበር በንብረትነቱ ሥር የሚገኘውን G+4 የፔንሲዮን (እንግዳማረፊያ) ሕንፃ እና መጋዝን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ማከራየት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

አጉንታ ተገጣጣሚ ቤቶች ኃ/የተ/የግ/ ማህበር በንብረትነቱ ሥር የሚገኘውን G+4 የፔንሲዮን (እንግዳማረፊያ) ሕንፃ እና መጋዝን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ማከራየት ይፈልጋል


Be'kur (Nov 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር አ.ተ.ቤ ግ/01/2010

አጉንታ ተገጣጣሚ ቤቶች ኃ/የተ/የግ/ ማህበር በንብረትነቱ ሥር የሚገኘውንና ከዚህ በታች የተገለጸውን G+4 የፔንሲዮን (እንግዳማረፊያ) ሕንፃ እና መጋዝን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ማከራየት ይፈልጋል፡፡

1. የኪራይና ንብረቱ ዝርዝር መግለጫ (Property Specifications)

ተ.ቁ

የንብረቱ ዓይነት እና መግለጫ

የሚገኝበት ቦታ አድራሻ

1

G+4 ሕንፃ ለፔንስዮን እንግዳ ማረፊያ አገልግሎት የተዘጋጀ ሙሉ መሠረት ልማት የተሟላለት

በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ጣና ከፍለ ከተማ ምድረ ገነት ቀበሌ ከቻይና ካምፕ ምዕራብ አቅጣጫ ቤተ ሰላም የእንግዳ ማረፊያ

2

ሰፊ የእቃ ማከማቻ መጋዝን Warehouse) ሙሉ በሙሉ ግንባታው የተጠናቀቀ፣ ለፔንሲዮን ወይም ለሆቴል አገልግሎት የተዘጋጀ፣ 74 መኝታ ክፍሎች ያለው

3

አጠቃላይ ግቢው የተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታ ያለው፣ ለተለያዩ ምርቶችና ዕቃዎች ማከማቻነት የሚያገለግል፣ ሰፊ የጭነት መኪና ማቆሚያና መግቢያ ያለው

 ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ዋና ዋና መስፈርቶች (Eligibility Criteria)

2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለጨረታ መወዳደር የሚያስችል የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የዋጋዉን መጠን 2 በመቶ በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን የፋይናንስ ሰነድ በታሸጉ ኢንቨሎፖ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡

የጨረታ ሰነድ አገዛዝ፣ አቀራረብ እና መክፈቻ (Submission & Opening)

1. ተጫራቾች በነፃ የጨረታ ሰነዱን ከአጉንታ ተገጣጣሚ ቤቶች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ መውስድ ይችላሉ፡፡

2. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ቀናት ድረስ ለድርጅቱ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 በአጉንታ ተገጣጣሚ ቤቶች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ዉስጥ ይከፈታል፡፡

4. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 18 70 51 80 /09 18 71 94 95 ደዉለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አጉንታ ተገጣጣሚ ቤቶች ኃ/የተ/የግ/ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *