Addis Zemen (Nov 02, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢት/ከ/መንግሥት የጋርዱላ ዞን ዲራሼ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት፡–
- 1. የጽሕፈት መሳሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃ
- 2. የደንብ ልብስ
- 3. የእንስሳት መድኃኒትና መገልገያ መሳሪያዎች እና የዶዘር ማሽን ከራይ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር Tin No ያላቸው፣
4. የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
5. የጨረታ ማስከበሪያ 50,000/ሃምሳ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ የሚችሉ፣
6. በእንስሳት መድኃኒትና መገልገያ መሳሪያ የሚወዳደሩ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የምትችሉ፣
7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዲራሼ ወረዳ ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት አለባቸው፡፡ የገዙትን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማዘጋጀት በሁለት የተለያዩ ፖስታ በማሸግ ኦርጅናሉ ላይ ኦርጅናል ኮፒው ላይ ኮፒ ብሎ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ በዚህ ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ 15ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው 15ኛው ቀን የዕረፍት/የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይገባል፡፡ ጨረታው በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋርዱላ ዞን ዲራሼ ወረዳ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 14 በ15ተኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
8. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ያለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም፡፡
9. ተወዳዳሪዎች ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሠረት ናሙና የማቅረብና አሸናፊዎች ለሚያቀርቡት ዕቃ 10% ለሦስት ወር የሚቆይ ዋስትና የማስያዝ ግዴታ አለባቸው፡፡
10. የጨረታዎቹ አሸናፊዎች ተለይተው ከተገለፀላቸው ከ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መግባት አለባቸው፡፡ ተሸናፊዎች ደግሞ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ መውሰድ ይችላሉ፡፡
11. አሸናፊዎች የሚያቀርቡትን ዕቃ እስከ ጋርዱላ ዞን ዲራሼ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡– ተወዳዳሪዎች የሚሞሉት ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከ90 ቀናት በታች መሆን እንደሌለበት አናሳስባለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ 0467 740 344/343 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ
የጋርዱላ ዞን ዲ/ወ/ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት