ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የኮምፒውተር እና ተዛማች እቃዎች ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የኮምፒውተር እና ተዛማች እቃዎች ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 03, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር EAር 002/2019

1. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የኮምፒውተር እና ተዛማች እቃዎች ግዥን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

2, ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 -11፡00 ድረስ “ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ ሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት አንድ ዋና /Original የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፤ ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት፡፡ በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

4. ተጫራቾች የኮምፒውተር እና ተዛማች እቃዎች ግዥ የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (Unconditional) ባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 208 ሲሆን፣ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን ህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ 4፡45 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ይሆናል::

6. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

7. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09-11-93-73-75 መጠቀም ይችላሉ፡፡

8. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *