በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ (ሎት 1)፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች (ሎት 2)፣ የፅዳት ዕቃዎች (ሎት 3)፣ የመኪና ዕቃዎች (ሎት 4) እና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን (ሎት 5) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ (ሎት 1)፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች (ሎት 2)፣ የፅዳት ዕቃዎች (ሎት 3)፣ የመኪና ዕቃዎች (ሎት 4) እና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን (ሎት 5) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 03, 2026)

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ፦ አሽ/ተሽ/ፍ/ቁ/ባ/አዲስ ከተማ/2019/001

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አዲስ ከተማ ቅርንጫ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ፦

  • ሎት 1. የደንብ ልብስ
  • ሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  • ሎት 3. የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት 4. የመኪና እቃዎች
  • ሎት 5 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

  • ንግድ ምዝገባ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር)፣ የዘመኑን ግብር የተከፈለበት ከሊራንስ፣ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ሰርተፍኬት፣ ለእያንዳንዱ ሎት ማቅረብ አለባችሁ ::
  • ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  • የጨረታ ሰነዱን ከአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አዲስ ከተማ ቅ/ጽ/ቤት ከአስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 29 ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ፡፡

ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያነት፦

  • ለሎት 1፣ 2፣ 3፣ 4 እና 5 ለእያንዳንዳቸው በተናጥል የብር 7,000.00 (ሰባት ሺህ ብር) CPO አሰርታችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል ፡፡

በለስልጣን መስሪያ ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፦ ከጳውሎስ ሆስፒታል ወረድ ብሎ ከመድሀኒአለም ት/ቤት ወደ ግሩም ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ

አዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ግቢ ውስጥ የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 29

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011-273-10-88-01-273-13-38 መጠየቅ ይቻላል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር

ባለስልጣን አዲስ ከተማ ቅርንጫ ጽ/ቤት