Be'kur (Nov 02, 2026)
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ፋይናንስ/ን/አስ ለሴክተር መ/ቤቶች
- ሎት 1. የአዳራሽ ወንበር ተከላ፣
- ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ እና
- ሎት 3. የጽዳት እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም መጫረት የምትፈልጉ ድርጅቶች ጨረታው በሎት በጥቅል መሆኑ አውቃችሁ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥዉ መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-4 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ተነባቢ በሆነ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተዳዳሪዎች የንግድ ፈቃዳቸው በሚጋብዛቸው ብቻ መወዳደር አለባቸው፡፡
- ተቋራጮቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ክፍለዉ ዳንግላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 13 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1. የአዳራሽ ወንበር ተከላ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር፣ ሎት 2. የኤሌክትሮኒክስ እቃ ብር 50,000 (አምሳ ሽህ ብር) እና ሎት 3. የጽዳት እቃ ብር 20,000 ሀያ ሽህ ብር) በኢትጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደ ምርጫችሁ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረስኝ ገቢ የሚያደርግ እና ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- አሸናፊ ድርጅቱ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዋጋ 10 በመቶ ዋስትና (በቢድ ቦንድ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (በሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ እና በመስሪያ ቤቱ የሂሳብ ቁጥር ገቢ ማድረግ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማ እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ኦሪጅናል እና ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ በግዥ/ፋይ/አስ/ቡድን ግዥዎች ቢሮ ለጨረታ ከተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 ቀናት እስከ 11፡00 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- በ21ኛዉ ቀን እስከ ረፋዱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ለጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ፡፡
- ጨረታው በ21ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በ4፡16 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በተጨማሪ በአብክመ የግዥ መመሪያ ቁጥር 144/2018 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- የተጠቀሰው እቃ ከተጠየቀው በ20 በመቶ ሊቀንስም ሊጨምርም ይችላል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር ሁኔታ ለመጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 221 16 10 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- አዳራሽ ወንበር ተከላው ላይ መሳተፍ ለምትፈልጉ ከደረጃ 4 እና በላይ በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ GC እና BC/ ያላቸው መሆን አለበት፡፡
የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት