Be'kur (Nov 02, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ደ/ታቦር ከተማ የሚገኘዉ የጎህ ሁለገብ የገ/ህ/ ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተወሰነ የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች ማለትም፡-
- ሎት 1. ፒፒሲ ሲሚንቶ ብዛት 500 ኩ/ል፣
- ሎት 2. የቆቦ አሸዋ ብዛት 144 ሜ/ኩብ፣
- ሎት 3.ዜሮ ዜሮ (00) ጠጠር ብዛት 56 ሜ/ኩ፣ 01(ዜሮ አንድ) ጠጠር ብዛት 80 ሜ/ኩብ እና 02 (ዜሮ ሁለት) ጠጠር ብዛት 136 ሜ/ኩ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች (ግለሰቦች) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩና የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (ዋስትና) ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በጎሕ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የግዥ ዋጋው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል (ሎት) እንጅ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) የሚገልጽ የጨረታ ሰነዱን እና የተጫራቾች መመሪያውን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከጎህ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ ቀርበው በመግዛት ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000561188126 ገቢ በማድረግ ኦርጅናል የባንክ አድቫይስ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ የመወዳደሪያ ዋጋ፣ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሰነዱን እና የተጫራቾች መመሪያውን በሚያሳውቁት የቴሌግራም አድራሻ ማስላክ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-5 የተዘረዘሩትን ሰነዶች ሞልተው በፖስታ በማሸግ በዩኒዬኑ ቢሮ በደ/ታቦር በጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ታቦር ዲስትሪክት ህንጻ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት በ5 ቀን ዉስጥ ያሸነፉትን የግንባታ ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መዉስድ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት /በምድብ/ ዋጋ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ አሸናፊ ይሆናል፡፡ ከሎት ውስጥ የአንዱን ዕቃ ዋጋ ካልሞሉ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን እስከ 6፡30 ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በ10ኛው ቀን መጨረሻ ከቀኑ 8፡30 ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡40 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- ዪኒየኑ ከሚገዛው የግንባታ ዕቃ ውስጥ 20 በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት አለው፡፡
- ዩኒዬኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በኀብረት ሥራ ማህበራት ግዥና ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 /058 141 99 27 ደዉሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ጎሕ ሁለገብ የገበ/ህ /ስ/ማህበራት ዩኒየን
ኃ.የተወሰነ