Be'kur (Nov 02, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ጤና ቢሮ የባሕር ዳር ከፍተኛ ትምህርት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አገልግሎት የሚውሉ በ2019 በጀት አመት የሚፈጸሙ የግዥ አይነቶች፡ -የጽህፈት መሳሪያዎች ሎት 1. ፣የጽዳት እቃዎች ሎት 2. ፣የደንብ ልብስ ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ እቃ ሎት 4፣ የጥገና እቃዎች ሎት 5.፣ ፈርኒቸር ሎት 6.፣medical supplies ሎት 7.፣ medical Equipments ሎት 8.፣ Chemicals and reagents ሎት 9.፣ Medications and supplies ሎት 10.፣ ህትመት ሎት 11.፣ የመኪና ማስዋቢያ እቃ ሎት 12.፣ እና የደንብ ልብስ ስፌት ሎት 13. በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ
መሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ - ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በየሎቱ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከግዥ ንብ/አስ/ደ/የስራ በሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 05 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚወዳዳሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ባሕር ዳር ከፍተኛ ትምህርት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ 16ተኛዉ ቀን 2፡30 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚሁ እለት 2፡31 ታሽጎ በዚሁ እለት 3፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ከመከፈት አያስተጓጉለውም፡፡ የመክፈቻው ቀን በዓል (ዝግ) ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ጨረታው በሎት ስለሚታይ ተጫራቾች ሁሉንም በሎቱ የተገለፁትን ዝርዝር መሙላት አለባቸው፡፡ ከሎቱ ውስጥ አንዱን ያልሞላ አጠቃላይ ከጨረታ ውድቅ ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ኮሌጁ ከፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል 100 ሜትር ገባ ብሎ ከኦክስጅን ማቀነባበሪያ ጎን ይገኛል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 058 220 07 71 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማሳሰቢያ፡- ዉድድሩ የሚካሄደዉ ጠቅላላ የሎቱ ድምር ስለሆነ ተወዳዳሪ ድርጅቶች በሰነዱ ላይ ያሉትን የእቃ ዝርዝሮች በሙሉ መሙላት ይጠበቅባችኋል፡፡
የባሕር ዳር ከፍተኛ ትምህርት
ጤና ሳይንስ ኮሌጅ