Addis Zemen (Nov 06, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር WSSF/PL/008/2026
የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መለዋዎጫዎች እና ግብአቶች በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ምድብ |
የእቃው አይነት |
|
1 |
የማሽነሪዎች እና የእርሻ ትራክተር ክራይ (BACK LOADER, EXCAVATOR, DOZER …..) |
|
2 |
የሰራተኛ ማመላለሻ አውቶቢስ ክራይ |
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ለእያንዳንዱ ምድብ ለየብቻ የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በኢትዮጰያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000473232708 በጨረታ ተሳታፊው ድርጅት ስም ገቢ በማድረግ ከላይ በተጠቀሱት ግዢዎች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ በመግዛት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ
ሜክሲኮ ፊሊንስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201
ለተጨማሪ መረጃ 011 558 5229 / 011 551 6082 / 09 84 55 0 101
አዲስ አበባ
2.ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር ቴክኒካ ዶክመንት ጋር የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የታክስ ክሊራንስ ሰርትፊኬት ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፤ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ፤ የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፊኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በየግዢ መጠይቁ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 15 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 6፡00 ከመሆኑ በፊት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
4. ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰአት ላይ ከላይ በተገለጸው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 201 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚሆን ሲሆን ትክክለኛው ቀን በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የሚጠቀስ ይሆናል።
5. ወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ