ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በንሳ ጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ፕሮጀከት ጉድጓድ የማስቆፈር ስራ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በንሳ ጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ፕሮጀከት ጉድጓድ የማስቆፈር ስራ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 06, 2026)

ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 01/209

የጨረታ ማስታወቂያ

ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በንሳ ጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ፕሮጀከት ጉድጓድ የማስቆፈር ስራ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች፦

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው

2. ቫት የተመዘገቡ

3. በጨረታ ለመሣተፍ ከገቢዎች ፍቃድ ያላቸው

4. የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል

የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ጊዜና ቦታ፦

1. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሂሳብ ቁጥር 1000604259658 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ የንግድ ፍቃዳቸውን ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ ሲዳማ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላሉ፣

ጨረታው የሚከፈትበት እና ሰነዱ የሚቀርብበት ጊዜ፦

1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ ከ8:30 እስከ 11፡00 ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ።

2. በማግስቱ በ16ኛው ቀን ከጧቱ ከ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

3. ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።

የጨረታ ዋስትና ፦

1. ማንኛውም ተጫራች 2% በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም ከስድስት ወር ያላነሰ ጊዜ ያለው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ቢድቦንድ ዋስትና ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል።

የጨረታ ሠነድ አስተሻሸግ ሁኔታ ፦

1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ፣ የልዩ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነትና የታክስ ክፍያ ማረጋገጫ ሰነዶች፣ በጨረታው ለመሳተፍ ከገቢዎች የተሰጠ ማስረጃ እና የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተደገፈ CPO/ ከኦርጂናል የዋጋ ማቅረቢያ ጋር በአንድ ላይ በሰም ታሽገው መቅረብ አለባቸው። ፋይናንሻል ዶኩሜንት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።

2. ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።

ይህንን አስተሻሸግ ዘዴ ያልተጠቀመ ተጫራች ከጨረታው ይሠረዛል።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 16 07 15 39 / 09 11 80 67 09 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡– ሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ዋናው ካምፓስ ፊት ለፊት መሆኑን እንገልጻለን።

ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *