ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አ/ማ የተለያዩ መለዋወጫ እቃዎች፣ የአዉቶቢስ ጎማና ባትሪዎች፣ የሞተር፣ የጊርቦክስና ዲፈረንሽያል ዘይት እና አዉቶሞቢል መኪኖችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አ/ማ የተለያዩ መለዋወጫ እቃዎች፣ የአዉቶቢስ ጎማና ባትሪዎች፣ የሞተር፣ የጊርቦክስና ዲፈረንሽያል ዘይት እና አዉቶሞቢል መኪኖችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 08, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አ/ማ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን መለዋወጫ እቃዎች የአዉቶቢስ ጎማና ባትሪዎች፣ የሞተር፣የጊርቦክስና ዲፈረንሽያል ዘይት እና አዉቶሞቢል መኪኖችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1 የዩቶንግ አዉቶብስ መለዋወጫ ዕቃዎች
  • ሎት 2. የሞተር፣የጊርቦክስና ዲፈረንሽያል ዘይት
  • ሎት 3. የአዉቶቢስ ጎማና ባትሪዎች
  • ሎት 4. አዉቶሞቢል መኪኖችን

ስለሆነም፡– አ/ማህበሩ ከላይ ከሎት 1 እስከ 4 የተገለፁትን ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ በጨረታው መወዳደር ለሚፈልግ ማንኛዉም ተጫራች ከዚህ በታች በተገለፀዉ የጨረታ መመሪያ መሠረት መሳተፍ ይችላል፡፡

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤የምዝገባ የምስክር ወረቀት ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ክሊራንስ የተሰጣቸዉ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት እና TIN ቲን ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸዉ፡፡

2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር ከ2፡30-11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ 2፡30-6፡30 ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ በአ/ማህበሩ ዋና መ/ቤት መስቀል አደባባይ ፊንፊኔ ህንፃ 6ተኛ ፎቅ ማግኘት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ንብረት የጨረታ ማስከበሪያ (bid bond) ለሚያቀርቡትን እቃ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ (CPO) በሰላም የህዝብ ማመላለሻ አ/ማ (Selam bus line share company) ስም አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ በድርጅቱ ጋራጅ ዉስጥ ለዚሁ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

5. ጨረታዉ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ9፡15 በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

6. ማንኛዉም ተጫራች የሚጫረትባቸዉን ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ (specification) ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ፕሮፖዛሎች በግልፅ በመጥቀስ ለየብቻ በማዘጋጀትና በማሸግ በተጨማሪ ሁለቱንም በአንድ ኢንቨሎፕ በማሸግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ፡፡

7. ከሎት3፣ሎት4 እና ከመስታዉቶች በስተቀር ለሁሉም እቃዎች ናሙና (sample) ጨረታዉ ከመዘጋቱ ከአንድ ቀን በፊት ቀድመው ዮሴፍ ቤ/ክርሲቲያን ፊት ለፊት በሚገኘዉ የድርጅቱ መጋዘን ማስገባት አለባቸው ናሙና ያልቀረበባቸዉ እቃዎች በጨረታው እንዳልቀረቡ ተቆጥሮ ዉድቅ ይደረጋሉ ወይም ፋይናንሽያል ውጤታቸው አይታይም፡፡

8. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተነገራቸው ወይም የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተላከላቸዉ ቀን ጀምሮ በ15 (በአስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናቶች ዉስጥ በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ በገዥዉ ድርጅት ቅጥር ግቢ ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፡– በስልክ ቁጥር 09-75-23-27-10 // 011-515-86-96 ደውለዉ ይጠይቁ፡፡

ሰላም የሕዝብ ማመላለሻ አ.ማ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *