Addis Zemen (Nov 10, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ለተለያዩ የመ/ቤቱ ስራ የሚውሉ መኪኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላል።
1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉት ከህዳር 04 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ኅዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰኞ እስከ ዓርብ በሥራ ሰዓት አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሥሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታውን ሠንድ በመግዛት መወዳደር ይቻላል።
2. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ወቅት የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ዋናውን እና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ውጤቱ እንደታወቀ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንከ ተረጋግጦ በሚቀርብ ዋስትና (CPO) 50,000 (ሀምሳ ሺህ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በጨረታው ሰነዶቻቸው ላይ የጨረታውን ስም፤ የተጫራቹን መሉ ስም እና አድራሻ በትክክል መጻፍ አለባቸው።
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኅዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለዉ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
7. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘገጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 022-111-0994 / 022-112-3550 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን