Addis Zemen (Nov 12, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት መይሙና ኑሪ ሰይድ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ ጀማል ደሳለኝ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 99724 በ8/3/2014 ዓ.ም እና በመ/ቁ 76584 በ15/10/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኦሮሚያ ክልል ቡራዩ ከተማ መልካ ገፈር ወረዳ ውስጥ በአዲስ አበባ የጋራ ህንፃ ማህበር ውስጥ በተጠሪ ስም በአቶ ጀማል ደሳለኝ ተመዝግቦ የሚገኝ ቤት የቤቱ ስፋት 72 ካ/ሜ ቤቱ G+3 ሆኖ እየተሰራ ያለመሆኑን ቤቱ በአዋሰኝ በምስራቅ ወ/ሮ ዴርዳኖስ በምዕራብ አየስ በቀለ በሰሜን ወ/ሮ ሰሊና በደቡብ መንገድ የሚያወስነው ሆኖ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 5,068,215.36 ( አምስት ሚሊዮን ስልሳ ስምንት ሺህ ሁለት መቶ አስራ አምስት ከ36/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ግዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ታህሳስ 5 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን ፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦምሆነ አሳንሶ C.P.O የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት C.P.O አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃጸም ጽ/ቤት