Addis Zemen (Nov 17, 2026)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019
በካፋ ዞን የጠሎ ወረዳ ኦዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመደበኛ በ2019 በጀት ዓመት ኦዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ለሚገነባው የመድኃኒት ማከማቻ መጋዘን ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል ።
በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚትፈልጉ ተጫራቾች
ሀ/ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃና በዘርፉ የታደሰ የንግድምዝገባና የስራ ፍቃድ
ለ/የቲን/Tin/ምዝገባ ወረቀትና የቫት ተመዝጋቢ የሆነና ሁሉ የወቅቱን ገቢያ ዋጋና በወቅቱ የምዝገባ ሰርተፍኬት
ሐ/ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
መ/ ከ2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ አሁን ለግንባታዎችም መልካም አፈፃፀም ደብዳቤ ማቅረብ የሚችልና የግንባታውን ስራ በገባው ውል መሰረት የሚያስረክብ
ሠ/ የግንባታውን ወቅት በተዳጋጋሚ ማስታወቂያ ያልወጣበት
ረ/ ተጫራቾች ግንባታ የሚገነባበት ከኦዳ ከመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሳይት ምልከታ ደብዳቤ ማቅረቡ አለባቸው ።
- ተጫራቾች ከ “ሀ” እሰከ “ረ” የተጠቀሱትን የንግድ ፍቃድ የቫትና የግብር ከፋይነትን መለያ ቁጥር እንዲሁም ሌሎች መረጃዎችን የጨረታ ዶክመንት ሲገዙ ኦርጅናሉንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግደታ አለባቸው ፡፡
- በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ የማይመለስ የሰነድ ሽያጭ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር)ብቻ በመከፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ለተከታታይ 30 የስራ ቀናት በካፋ ዞን የጠሎ ወረዳ ኦዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ንብ/አስ/ር በመቅረብ መግዛት ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ በባንክ በተረጋገጠለት ሲ.ፒ.ኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ጠሎ ወረዳ ኦዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ንብ/ አስተዳደር ብር 100,000.00/ አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ ከጨረታው ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዘው ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም/በሙጫ/በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 የስራ ቀናት በካፋ ዞን የጠሎ ወረዳ ኦዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ንብ/አሰ/ር በመቅረብ ለዚሁ ስራ ለተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥማስገባት ይችላሉ ።
- ግንባታዎች ፍቃዳቸው BC/GC/ ደረጃ 6 እና ከ6 በላይ /አሸዋ ኛ ደረጃ መሆን አለበት ።
- በገቡበት ውል መሰረት ጊዜና ቀናትን ጠብቀው ሰረተው ማስረከብ የሚችል እና ከዚህ ቀደም የግንባታ ውል ያላቋረጡ መሆን አለባቸው ።
- የመሃንዲስ አስተያየት ተቀብሎ ለመስራትና በሚሰጠው አስተያየት ተገቢውን ስራን ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ
- የጨረታው ሳጥን በ30ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትበቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ሂደት አለመገኘት ጨረታውን አያስተጓጉልም፡፡
- ከዋጋ ጥናቱ ከ5% በታች በሆነ ዋጋ ጨረታ የሚያሸንፍ ተወዳደሪ ያለቅድመ ክፍያ ስራ ይጀምራል። እንዲሁም የውል ማስከበሪያ 20% የሚያሲይዝ መሆኑን እንገልፃለን :: በተደረገው የሂሳብ ስህተት ማስተካከያ / Arithmetic error /የመጣው ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ መክፈቻ ስነ–ሰርዓት ላይ ከተነበበው ጠቅላላ ዋጋ ከ2% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ ከሆነ የተወዳዳሪው ሰነድ ውድቅ ይደረጋል ። እስካሁን በዞን ደረጃ ግንባታ ስራላይ ተጫርተው አሸናፊ ሆነው ስራውን እየሰሩ ያሉት አፈፃፀማቸው ከ70 % በላይ
- መሆናቸውን ከአሠሪ መ/ቤት የድጋፍ ደብደቤ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ።
- የመክፈቻው ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ 0917403723/0976802922/0917190831/0925163248 ደውለው ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ ።
የጠሎ ወረዳ ኦዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል