ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽሕፈት ቤት የከሶኮል ወንዝ ድልድይ ግንባታ እና የኤሲኒ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ለደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ GC/RC/ የሆኑ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽሕፈት ቤት የከሶኮል ወንዝ ድልድይ ግንባታ እና የኤሲኒ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ለደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ GC/RC/ የሆኑ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 19, 2026)

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በከተማው ውስጥ የተለያዩ የግንባታ ስራዎች

  • ሎት 1፡– የከሶኮል ወንዝ ድልድይ ግንባታ/ በዲያቢ መንደር ያለው/
  • ሎት 2፡– የኤሲኒ ወንዝ ድልድይ ግንባታ /ከአቶ ሁሴን መሐመድ ቤት አጠገብ/

ግንባታ ለደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ GC/RC/ የሆኑ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተቋራጮች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ

  1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው::
  3. በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ኦንላይን የተመዘገቡና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
  5. ግብር ስለመከፈላቸው ከገቢዎች መቤት ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6.  የጨረታ ሰነድ ከግዥ ንብ/አስ/ር የሥራ ሂደት ቢሮ 2,000/ሁለት ሺ ብር ከፍለው በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱ ሞልተው ሲመልሱ ቴክኒካሉን 1 ኦርጅናልና 2 ኮፒ ፋይናንሻሉን 1 ኦርጅናልና 2 ኮፒ በሁለት ፖስታ በማድረግ እና በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስባት ይኖርባቸዋል፡
  8.  የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ 190,000 (አንድ መቶ ዘጠና ሺ ብር) ለሎት ሁለት 170,000/ አንድ መቶ ሰባ ሺ ብር ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ቼክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ለሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በማለት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ22ኛዉ ቀን ሎት አንድ ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡00 ሠዓት፣ ሎት ሁለት 8፡30 ታሽጎ 9፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ይሆናል፡፡
  10. ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው
  11. በጨረታ ማስታወቂያ ላይ የቃላት ወይም የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጠው የበለጠ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ሚ/ኣ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *