የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለደባርቅ ቧሂት የመንገድ ስራ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የ(Asphalt RC-70) ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለደባርቅ ቧሂት የመንገድ ስራ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የ(Asphalt RC-70) ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 19, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCE/01/167/2026

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለደባርቅ ቧሂት የመንገድ ስራ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተጠቀሰውን የ(Asphalt RC-70) ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የዕቃው አይነት

የፕሮጀክት ስም

የጨረታ ቁፕር

 

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን ሰዓት

የጨረታ ማስከበሪያ

 

1

(Asphalt RC-70)

ሊደባርቅ ቧሂት የመንገድ ስራ ፕሮጀክት

DCE/Ol/67/2026

ህዳር 21/2019 ዓ.ም 8፡15 ሰዓት

 

ህዳር 21/2019 ዓ.ም 8፡30

 

500,000.00

 

ስለሆነም፡-

1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ… ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ (Bid Bond) 120 ቀን ፀንቶ የሚቆይ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የመድን ድርጅቶች ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።

3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር/ በመክፈል ዘውትር በሥራ ሰዓት የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት አዲሱ ቢሮ ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ ውስጥ።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የገዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34

ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72

E-mail አድራሻ Info@dee-et.com

የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com 

ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝፕራይዝ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *