Addis Zemen (Nov 23, 2026)
የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶች ግዥ
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ 13/2019
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ከታች በሎት የተዘረዘሩትን ግብዓቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የወንዝ አሸዋ ከነትራንስፖርቱ
- ሎት 2 ቀይ አሸዋ ከነትራንስፖርቱ
- ሎት 3 ሀርድ ኮር ከነትራንስፖርቱ
- ሎት 4 ሰሌክት ማቴሪያል ከነትራንስፖርቱ
- ሎት 5 ፑሚስ ከነትራንስፖርቱ
ስለሆነም
1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት፣ የንግድ ምዝገባ፣ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለእያንዳንዱ ሎት 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ከታወቀ ባንከ የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና (unconditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከሰዓት 8፡30 ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
4. የኮንስትራከሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት