Be'kur (Nov 23, 2026)
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሳሽ ሙሉጌታ አምሳል እና በአፈ/ተከሳሽ እነ ደሳለው ሽቴ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ፤ በአገው ግምጃ ቤት፣ ቀበሌ 01 በሰሜን የቀበሌ ቤት፣ በደቡብ መንገድ፣ በምስራቅ ግርማው አለማየሁ እንዲሁም በምዕራብ ተስፋየ ብዙየሁ መካከል ተዋስኖ የሚገኘው፤ በአቶ ደሳለው ሽቴ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው በመነሻ ዋጋ 983‚010 (ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ሺህ አስር ብር) ይሸጣል፡፡ በመሆኑም የጨረታ ማስታወቂያው ከህዳር 14/2019 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 14/2019 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 30 ቀናት ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ቆይቶ ታህሳስ 16/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ይሸጣል፤ ተጫራቾች ወደ ጨረታው ሲመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ኛውን በሲፒኦ አስይዛችሁ እንድትቀርቡ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባንጃ ወ/ፍ/ቤት