Be'kur (Nov 23, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2019 በጀት አመት በዞኑ ስር ለሚገኙት መምሪያዎች አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1. እስቴሽነሪ እና ሌሎች እቃዎች ፣
- ሎት 2. የጽዳት እቃዎች፣
- ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር እቃዎችን በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።
- የግብር ከፋይ የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የግብር ኪሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱትን የግዥ መጠን ብር ከ500,000 (አምስት መቶ ሽህ) ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ለስቴሸነሪ ፣ኤሌክትሮኒክስ ዋጋ 50,000 (ሃምሳ ሽህ ብር) እና የጽዳት እቃ እና ፈርኒቸር 15,000 (አስራ አምስት ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ መሂ 1 በማስያዝ ጨረታው እስከ ሚዘጋበት ሰዓት ድረስ ግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ውስጥ ወይም ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም የሚያስይዙት ዋስትና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቹ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በማያያዝ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከሰ/ጎ/ዞን ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ የተሞላበት ሳይኖረው ኦርጂናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡ ሆኖም ስርዝ ድልዝ ካላው ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
- ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ የሚቆይበት ጊዜ ከህዳር 14/2019 እስከ ህዳር 23/2019 ዓ.ም ለ10 ተከታታይ ቀናት ይሆናል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ህዳር 24/2019 ዓ.ም በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል።
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን እቃዎች የሚያቀርበው ለሰ/ጎ/ዞን ንብረት ክፍል የሚያስረክብ ይሆናል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው። የጨረታ ውድድር የሚካሄደው በሎት ድምር ይሆናል።
- የጨረታው መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ ይሆናል።
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 1 ዘወትር በስራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 41 72 544/058 41 70 126 መጠየቅ ይችላሉ።
የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ