በመካነ እየሱስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለዐቃቢ ህግ የቢሮ ግንባታና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል


Be'kur (Nov 23, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በመካነ እየሱስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለዐቃቢ ህግ የቢሮ ግንባታና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡

የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለውና የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግንባታውን ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔሲፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  4. ተጫራቾች በዝርዝር መግለጫው የቀረቡትን ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው፡፡
  5. የጨረታው ሰነድ ከህዳር 14/2019 ዓ/ም እስከ 24/2019 ዓ/ም ድረስ ዘወትር በስራ ስዓት ከጠዋት 1፡30 እስከ 6፡30 እና ከስዓት ከ9፡00 እስከ 12፡00 ድረስ በመ/ዮ/ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በመገኘት የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የአንድ ሰነድ መግዣ ዋጋ ብር 500( አምስት መቶ ብር ) መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  7. ተጫራቾች ለሚወዳድሩበት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የግባታውን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱ በመ/ዬ/ገ/ጽ/ቤት በግ/ፋ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 02 በቀን 25/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 የታሸገዉ ፖስታ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀን ተጫራቾች ባይገኙም የማይስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታዉ ሂደት በሚተላለፉ ዉሳኔዎች ተገዥ የሚሆን/የምትሆን፡፡
  9. አሸናፊው ተጫራች ውል የሚወስደው በመ/ዮ/ከ/አስ/ዐቃቢ ህግ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 18 73 78 03 የሞባይል ቁጥር 09 18 73 77 76 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የመካነ እየሱስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *