Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል እንዲሁም ለንግድ አገልግሎት የሚውል ንብረቶች በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Aug 17, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሐራጅ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና 216/1992 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን የብድር መያዣ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
ቅርንጫፍ
|
የንብረት አስያዥ ስም |
የመያዣ ንብረቱ መለያ |
የሐራጁ መነሻ ዋጋ (ብር)
|
ሐራጁ የሚከናወንበት |
||||
አድራሻ |
የይዞታው ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር |
የይዞታው ስፋት (በ ካ.ሜ)
|
የይዞታው አይነት/የሚሰጠው አገልግሎት |
ቀን |
ሰዓት |
|||||
1 |
አቶ ማሩ ሩፎ ጉቴ |
ሚችሌ ቅ/ፍ |
ተበዳሪው |
ዲላ ከተማ፣ ሀሮ ወላቡ ክ/ከተማ ፣ሀሴዴላ ቀበሌ |
2881/2000
|
387 ካ.ሜ
|
ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል
|
2,353,524.26
|
07/01/2018 ዓ.ም |
3፡00_4፡00 ጠዋት |
2 |
አቶ ማሩ ሩፎ ጉቴ |
ሚችሌ ቅ/ፍ |
ተበዳሪው |
ዲላ ከተማ፣ ሀሮ ወላቡ ክ/ከተማ ፣ሀሴዴላ ቀበሌ |
2456/2002
|
450 ካ.ሜ
|
ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል
|
3,042,897.63 |
07/01/2018 ዓ.ም |
4፡00_5፡00 ጠዋት |
3 |
አቶ ማሩ ሩፎ ጉቴ |
ሚችሌ ቅ/ፍ |
አቶ ታምራት ማሩ ሩፎ |
ዲላ ከተማ፣ ሀሮ ወላቡ ክ/ከተማ ፣ሀሴዴላ ቀበሌ |
00014/2001
|
474 ካ.ሜ
|
ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል
|
2,890,565.08 |
07/01/2018 ዓ.ም |
5፡00 –6:00 |
4 |
አቶ ማሩ ሩፎ ጉቴ |
ሚችሌ ቅ/ፍ |
አቶ ኤፍሬም ማሩ ሩፎ |
ዲላ ከተማ፣ ሀሮ ወላቡ ክ/ከተማ ፣ሀሴዴላ ቀበሌ |
8911/2011 |
1332.40 ካ.ሜ |
ለንግድ አገልግሎት የሚውል
|
9,597,304.32 |
07/01/2018 ዓ.ም |
8፡00_9፡00 ከሰዓት |
5 |
አቶ ማሩ ሩፎ ጉቴ |
ሚችሌ ቅ/ፍ |
ወ/ሪት አታለለች ማሩ ሩፎ |
ዲላ ከተማ፣ ሀሮ ወላቡ ክ/ከተማ ፣ሀሴዴላ ቀበሌ |
477/2013 |
178 ካ.ሜ |
ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል
|
1,038,341.09 |
07/01/2018 ዓ.ም |
9፡00_10፡00 ከሰዓት |
በመሆኑም
1. ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛውን በባንክ በተረጋጋጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይቻላል።
2. የንግድ ማሕበራትን ወክሎ ለመጫረት የማሕበራቱን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበራቱ ስም ንበረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ ስነድ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
3. ሐራጁ ዲላ ዲስትሪክት በሚገኘው የባንኩ ህንፃ በምድር ወለል ላይ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ የሚከናወን ይሆናል።
4. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈው ንብረት ላይ በህጉ አግባብ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የሚከፈል ከሆነ ይህንኑ ታስቦ የሚከፍል ይሆናል።
5. የጨረታ አሸናፊ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያው በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልተፈፀመ ጨረታው ተሰርዞ ለሐራጅ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ተመላሽ አይደረግም።
6. ንብረቱን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ሰዓት ንብረቱን በሚገኝበት አድራሻ በመገኘት ወይም ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይችላሉ።
7. ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልከ ቁጥር 046- 131-0905፣ 046-131-7311 በመደወል ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲላ ዲስትሪክ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የህግ ክፍል በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲላ ዲስትሪክት