Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ከ2025 እ.ኤ.አ በጀት ዓመት ጀምሮ ለ3 ዓመታት የድርጅቱን ሂሳብ ኦዲት የሚያደርጉ ተገቢውን መስፈርት የሚያሟሉ የኦዲት ድርጅቶችን አወዳድሮ የአገልግሎት ስምምነት መፈጸምና ማሰራት ይፈልጋል
Reporter(Aug 17, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ)
Ethiopian Human Rights Council (EHRCO)
የውጭ ኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሆኖ በምዝገባ ቁጥር 1146 ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ መንግስታዊ ያልሆነ ከፖለቲካና ከሐይማኖት ወገንተኝነት ነፃ የሆነ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሲሆን ከ2025 እ.ኤ.አ በጀት ዓመት ጀምሮ ለ3 ዓመታት የድርጅቱን ሂሳብ ኦዲት የሚያደርጉ ተገቢውን መስፈርት የሚያሟሉ የኦዲት ድርጅቶችን አወዳድሮ የአገልግሎት ስምምነት መፈጸምና ማሰራት ይፈልጋል።
የማመልከቻ መስፈርቶች፡–
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤
- የግብር መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት፤
- ለዓመቱ (2025፣ 2026 እና 2027) ለአገልግሎት የሚጠይቁትን ክፍያ ዋጋ፤
- የአለም አቀፍ የህዝብ ሴክተር የሂሳብ አያያዝ ደረጃዎች (PSAS) በቂ የኦዲት ልምድ ያለው፤
- የበጀት ዓመቱ የኦዲት ሥራውን የሚያጠናቅቁበት ጊዜ፤
- በተመሳሳይ ተቋማት ላይ በቂ የኦዲት ልምድ ያለው እና በኦዲት ተቋማት ላይ የተጣለውን የህግ ግዴታ የሚያሟላ፤
ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ የኦዲት ድርጅቶች በሚከተለው አድራሻ ሰነዶቻችሁን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 የሥራ ቀናት ውስጥ ከታች በተቀመጠው ኢሜይል አድራሻ በማመልከት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ኢሜይል– Info@ehrco.org
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር +251 90 159 4327 ወይም + 251 91 036 9497 ይደውሉ