Your cart is currently empty!
በደቡብ ኢ/ክ መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የግሬደር ጎማ ግዥ እና የዶዘር ማሽን ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 18, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢ/ክ መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ከደን ሽያጭ በተገኝ ገንዘብ በጋርዱላ ደን ውስጥ ለውስጥ መንገድ ለማስከፈት –
- የግሬደር ጎማ ግዥ እና
- የዶዘር ማሽን ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር TIn No ያላቸው
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው
- የጨረታ ማስከበሪያ የግሬደር ጎማ ግዥ 16,000 /አስራ ስድስት ሺህ ብር/ የዶዘር ማሸን ኪራይ 30,000 ሰላላ ሺህ ብር ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ሲፒአ ወይም የባንክ ዋስትና ለዓሳ ዘጠና ቀናት የሚቆይ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከጋርዱላ ዞን ገቢዎች ጽቤት በመቅረብ የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት አለባቸው።
- ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማዘጋጀት በሁለት የተለያዩ ፖስታ በማሸግ ኦርጅናሉ ላይ ኦርጅናል ኮፒው ላይ ኮፒ ብሎ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማሳረፍ በዚህ ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ16 ተከታታይ ቀናት ወስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው። 16ኛው ቀን መደበኛ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይገባል፡፡
- ጨረታው በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ከፍል ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ያለመገኘት የጨረውን አከፋፈት እያስተጓጉልም!
- ጨረታዎቹ አሸናፊዎች ተለይተው ከተገለፀላቸው ከ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ከባድ ችግር ካልተፈጠረ በስተቀር በ5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መግባት አለባቸው፡ ተሸናፊዎች ደግሞ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የግሬደር ጎማ ግዥ አሸናፊ የሚያቀርቡትን ጎማ እስከ ጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ መጋዘን ድረስ ማቅረብ አለበት የዶዘር ማሸን ኪራይ አሸናፊ እስከ መንገድ ከፈታ ቦታ ድረስ ዶዘሩን ማድረስና ሥራውን በገባው ውል መሠረት መሥራት አለበት፣
- የዶዘር ማሸን ኪራይ አሸናፊ የዶዘሩን የዘይት ሰርቪስና ጥግና ወጭ በራሱ ይሸፈናል፡፡
- መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር: 046 774 0344 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በደቡብ ኢ/ክ መንግሥት የጋርዱላ ዞን
ፋይናንስ መምሪያ