Your cart is currently empty!
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብ/ዞን የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የመኪና ጎማ፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የእንስሳት መድሃኒት፣ እና የእንስሳት ህክምና አላቂ ዕቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብ/ዞን የአርጡማ ፉርስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት አመት የተጠቃለለ ግዥ ከዚህ በታች በተቀመጡት የጨረታ ሰነድ የሎት ምድብ በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የመኪና ጎማ ግዥ፣
- ሎት 2 የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ፣
- ሎት 3 የእንስሳት መድሃኒት ግዥ፣
- ሎት 4 የእንስሳት ህክምና አላቂ ዕቃዎች ግዥ፣
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች
- በሚወዳደሩበት ዘርፍ የዘመኑ ግብር የከፈሉና የተሟላ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የTIN No ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የንግድ ምዝገባ ቁጥርና የተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሀሳብ መስጫ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሸያ ማድረግ አይቻልም፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ሆኖ ለወደፊት በመንግስት የሚወጣ ጨረታ እንዳይሳተፉ ሊደረግ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከዋና ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ
- የሚገዙትን ማቴሪያሎች ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ፤ የጨረታ ማስከበሪያ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመቀበያ ደረሰኝ በአ/ፉ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በምርጫቸው በአንዱ ከዋና /original/ የመወዳደርያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ብቻ ለብቻ ከሁሉም የንግድ ማስረጃዎቻቸው ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ከ13/12/2017 ዓ.ም እስከ 27/12/2017 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ለ15 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን 16 ኛው ቀን ማለትም 28/12/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት የሚታሸግ ይሆናል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ማለትም ከ28/12/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡30 በአ/ፉ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 በግልፅ የሚከፈት ሲሆን ምናልባት 16ኛው ቀን የህዝብ በዓል ወይም ከመንግስት የስራ ቀን ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾችጨረታው በሚከፈትበትሠዓትየንግድፍቃድናሁሉንምማስረጃዎቻቸውን ኦርጅናሉንና የማይመለስ አንድ አንድ ኮፒ ጋር ይዘው መገኘት አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ ግዥውን የሚፈጽመው በሎትም ሆነ በተናጠል አማራጩን ይዞ በጥራትም ሆነ በዋጋ ብቁ መሆናቸውን አረጋግጦ የመረጣቸውን ብቻ ሲሆን ከሚፈለጉት እቃዎች መካከል ለከፊሎቹ ብቻ ዋጋ መስጠት ተቀባይነት ላያገኝ ይችላል፡፡
- መ/ቤቱ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 033 449 0061 ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻን ጨፋ ሮቢት ከተማ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መስመር 300 ኪ/ሜ ላይ እንገኛለን።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብ/ዞን
የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት