ሄልቬታስ ስዊዝ ኢንተርኮኦፐሬሽን የግብርና ቴክኖሎጅ ማሽነሪ መግዛት ይፈልጋል


Reporter(Aug 20, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

በድጋሜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ሄልቬታስ ስዊዝ ኢንተርኮኦፐሬሽን በኢትዮጵያ በአማራ በኦሮሚና ክልሎች በስራ እድል ፈጠራ በግብርናና በአየር ንብረት ለውጥ በመሰረተ-ልማት ግንባታ በውሃ ስራዎችና በሌሎች ዘላቂና ጊዚያዊ የህይወት አድን ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ አለም አቀፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ነው በኢትዮጵያም ውስጥ መንግስት የቀረጻቸውን የልማት ፖሊሲዎች በመከተል ለአመታት በርካታ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል አሁንም በማከናወን ላይ ይገኛል።

የሄልቨታስ ኢትዮጵያ የሰቆጣ የአየር ንብረት መላመድ የግብርና አገልግሎት ፕሮጀክት በዋግ ኽምራ በስድስቱ ወረዳዎች የሚተገበር ተፋሰስን መሰረት ያደረገ የተሻሻሉ የግብርና ስራዎች በመተግበር የተለያዩ ማሽነሪዎች በማሰራጨት የአ ደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሻሻል የሚሰራ ፕሮጀክት ነዉ::በመሆኑም የሄልቬታስ ስዊዝ ኢንተርኮኦፐሬሽን በኢትዬጵያ ሰቆጣ ፕሮጀክት ኦፊስ በዋግ ኽምራ ዞን ላሉ አርሶ-አደሮች ተደራሽ የሚሆኑ የግብርና ቴክኖሎጅ እቃዎችን ለመወዳደር ፈቃደኛ እና ብቁ የሆኑ ሕጋዊ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

በጨረታው የሚፈለጉ የግብርና ቴክኖሎጅ እቃዎች

.

 

የግብርና ቴክኖሎጅ ማሽነሪው ዓይነት (Description of Agricultural technology Materials

መለኪያ

ብዛት

 

ተጨማሪ ማብራሪያ

 

1

Soil Moisture Tester

በቁጥር

30

 

2

Soil Moisture Conservation plough

በቁጥር

 

30

 

 

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች

  1. ጨረታውን ለመወዳደር ፍላጎት ያለውና የ2017 ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው
  2. የኢንዱስትሪ፡የግብርናና ኮንስትራክሽን መሳሪያዎችና መገልገያዎች ንግድ ፍቃድ ያለው።
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
  4. የግብር ክሊራንስ ያላቸው ብቁና ህጋዊ ሠውነት ያላቸው ተጫራቾች መሆን ይጠበቅባቸዋል።

መሟላት የሚገባቸው ጉዳዮች

  • ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋጋ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ብር 2% በሲፒኦ ለሄልቬታስ ስዊዝ ኢንተርኮኦፐሬሽን ሰቆጣ ፕሮጀክት ጽ/ቤት፣ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል
  • ፍላጎት ያላቸውና ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከቀን 14/12/2017 ዓ.ም እስከ 27/12/2017 ዓ.ም ወይም (እ.ኤ.አ ከቀን 20/08/2025 እስከ 02/09/2025) ድረስ ሰቆጣ ሄልቬታስ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ግዠ ክፍል ቢሮ ቁጥር 7 እና 8 ወይም በመቀሌ ሄልቬታስ ፕሮጄክት ጽ/ ቤት (አድራሻ መቐለ 22 አዲ ሃውሲ አዲ ሃቂ ወረዳ ሊባኖስ ሆቴል ፊት ለፊት በመምጣት የማይመለስ 700 ብር በመክፍል መውሰድ ይችላሉ።
  • የጨረታ ሰነዱን በ 28/12/2017 ዓ.ም (እ.ኤ.አ 03/09/2025) ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡30 ሰዓት ድረስ በሄልቬታስ ስዊዝ ኢንተርኮኦፖሬሽን ሰቆጣ ፕሮጀክት ጽ/ ቤት ከተዘጋጄው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
    ከተገለጸዉ ሰአት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተጫራች ተቀባይነት የለውም።
  • ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ 28/12/2017 ዓ.ም (እ.ኤ.አ 03/09/2025) ከ ሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት መሆኑን እያሳወቅን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ ሰቆጣ ሄልቬታስ ስዊዝ ኢንተርኮኦፖሬሽን ሰቆጣ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፡-

  • በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር እና ሲሞላ “ጠቅላላ ዋጋው የተሞላው ከቫት ጋር ወይም ቫትን ሳይጨምር ነው የተሞላው” የሚል ቃል መጨመር ከጨረታው ውድድር ውጭ ያደርጋል።
  • በእያንዳንዱ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒዎች ማረጋገጫ ሲቀርብ ለአስተማማኝነቱ ግልፅ በሆነ አጻጻፍ ታሽጎ በማህተም ተመትቶ መቅረብ አለበት።
  • ለ ሶስተኛ ወገን ኮንትራት አሳልፎ መስጠት በጥብቅ የተከለከለ ነው:: የድርጅቱን ስም የሚያጎድፉ ተግባራትን አለማድረግ፤ ለምሳሌ የቀን ሰራተኞችን ቅሬታ ማስነሳት/ ደሞዝ አለመክፈል ከአካባቢው ሰወች ጋር ተስማምቶ አለመስራት እና ህጻናትን ና ሴቶችን የሚጎዱ ነገሮችን ማድረግ የተከለከለ ነው:: ኦሪጅናል እና ኮፒ ተሟልተው ያልቀረበባቸው መረጃወች /ደኩመንቶች/ሙሉ በሙሉ ውድቅ ይሆናሉ።
  • የቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንቶች በኦርጀናልና ኮፒ በሚል ጽሁፍ መቅረብ ይኖርበታል።
  • የማይነበብ ፅሁፍ ወይም ድልዝ ደኩመንት በጨረታው ሂደት ውድቅ ይሆናል:: የስራ ልምድ በድርጅት ስም ሳይጻፍ ቀርቶ በግለሰቡ ስም ተጽፎ ቢቀርብ ተቀባይነት አይኖረውም።
  • ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *