Your cart is currently empty!
የፍቅር ልጆች ማህበር /Daughters of Charity/ ትግራይ ማስተባበርያ ጽህፈት ቤት የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተከርስቲያን – የልማትና ማህበራዊ ኮሚሽን ዓዲግራት ቅርንጫፍ /Ethiopian Catholic Church Social and Development Commission of Adigrat Branch/ ለተማሪዎች የምገባ ፕሮግራምና የምግብ እጥረት ላለባቸው ሴቶችና ህፃናት አገልግሎት የሚውል ፋፋ /Famix MS 5%/ በግልፅ ጨረታ አወዳድረን ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የፍቅር ልጆች ማህበር /Daughters of Charity/ ትግራይ ማስተባበርያ ጽህፈት ቤት የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተከርስቲያን – የልማትና ማህበራዊ ኮሚሽን ዓዲግራት ቅርንጫፍ /Ethiopian Catholic Church Social and Development Commission of Adigrat Branch/ ስር ሆኖ ለሚሰራቸው የተለያዩ የልማት፤ ማህበራዊና ሌሎች የሰብአዊ አገልግሎቶች አርዳታ እየሰጠ ይገኛል፤ ከሜርስ ሚልስ ዓለም አቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅት /MMI/ ጋር በመተባበር በ20 ወረዳዎች ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ያሉ በርካታ ተማሪዎች የሀገር ምርት በሆነ የምግብ ዓይነት ቀን አንድ ጊዜ የመመገብ ሰራ በመስራት ላይ ይገኛል።
ድርጅታችን ለተማሪዎች የምገባ ፕሮግራምና የምግብ እጥረት ላለባቸው ሴቶችና ህፃናት አገልግሎት የሚውል ፋፋ /Famix MS 5%/ በግልፅ ጨረታ አወዳድረን ለመግዛት ስለፈለግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ፋብሪካዎች እንድትወዳደሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
1. ፋፋ /Famix MS 5%/ ለማምረት የ2017 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ።
2. ቫት ተመዝጋቢ የሆነ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውና ህጋዊ ተከታታይ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል።
3. ተጫራቾች ለምርቱ የብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፍኬትና በቀን ፋፋ የማምረት አቅም ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው
4. ተጫራቾቸ ጨረታው ከተከፈተበት በኋላ ማስተካከያ ማድረግ፤ ራስን ከጨረታ ማግለልም ሆነ መቀየር አይቻልም።
5. ተጫራቾች ውል ከማሰራችን በፊት አጠቃላይ የፋብሪካው ደረጃና የማምረት አቅም ምዘና አንደምናካሂድ ማወቅ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች ጨረታ ማስከበርያ በ CPO 50,000.00 ብር በድርጅታችን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
7. ጨረታውን ያሸነፈ ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ውል ካሰረበት ቀን ጀምሮ ለስድስት ወር መሆኑ ማወቅ አለባቸው።
8. ተጫራቾች ዋጋ የሚያቀርቡትና ውል የሚያስሩት ለአንድ ኩንታል ቢሆንም በሚታዘዘው መጠን (Order) መሰረት የተጠየቀውን ሁሉ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
9. ጨረታ ያሸነፈው ምርቱ አዲስና ቢያንስ 6 ወር የአገልግሎት ጊዜ ያለው በውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ፕላስቲክ ከላይ ደረጃውን የጠበቀ በ50 ኪ/ግ ማሸግያ በመጠቀም የድርጅታችን 3 ሎጎዎችንና በቻ ቁጥር በማተም ማቅረብ የሚችል።
10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መቀለ ዓዲ ሓቂ ከፍለ ከተማ ካቶሊክ የዓይን ህከምና በስተጀርባ የሚገኘው የፍቅር ልጆች ማህበር ትግራይ ክልል ማስተባበርያ ጽህፈት ቤት ወይም አዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የቤት ቁጥር 374 ካቴድራል ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ከ 12/12/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 20/12/2017 ዓ.ም ድረስ መውሰድ ይችላሉ።
11. ጨረታው በመቀለ በዋና ፅህፈት ቤት በ 20/12/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 9፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ ሆኖም ተጫራቾች ባይኖሩም ጨረታው ይከፈታል።
12. የፍቅር ልጆች ማህበር ትግራይ ማስተባበርያ ጽህፈት ቤት ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ ማሳሰቢያ የዋጋ ማቅረቢያ ቅጅ ከአዲስ አበባ ጽ/ቤት መውሰድ ይቻላል።
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የልማትና ማህበራዊ ኮሚሽን ዓዲግራት ቅርንጫፍ
የፍቅር ልጆች ማህበር / Daughters of Charity/ ትግራይ ማስተባበርያ ጽህፈት ቤት