የአብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የመኪና እቃ ግዥ በግለጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 20, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ ህ/ጤ/ኢ/ወ/ቅ የገልጽ ጨረታ ቁጥር 001/2017

የአብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢስቲትዩት ወልድያ ቅርጫፍ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል  የመኪና እቃ ግዥ በግለጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. የግብር መክፈያ ቁጥር /ቲን ነበርያ ያላቸው : ግዥው ከ200,000/ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና ማቅረብ የሚችል።
  3. ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተም፣ ፊርማና ስም በሚነበብ መልኩ መጻፍና በየገጹ ማህተም ማድረግና መፈረም ይጠበቅባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ግብር እና ታክስን ያካተተ ዋጋ መሆን አለበት።
  5. ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ በፖስታ አሽገው ማቅረብ እና በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ውድድሩ በድምር ዋጋ ወይም በሎት መሆኑ ታውቆ ሁሉንም መሙላት አለባቸው።
  7. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት መጥተው ውል መውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀነ ገደብ በውሉ መሰረት መፈጸም አለበት።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ተጫራቾች ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል ገዝተው መውሰድ ይችላሉ ።
  9. የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  10. በጨረታው ያልተገኙ ተጫራች ፖስታው በሌሉበት የሚከፈት ሆኖ በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተገዥ ይሆናል።
  11. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማብራሪያ ጥያቴ ካላቸው ከጨረታ መክፈቻ ጊዜው ከ5 ቀን በፊት ለኢንስቲትዩቱ ቅርንጫፍ ማሳውቅ አለበት።
  12. የጨረታ ማስከበሪያ የዋሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በሲፒኦ፣ በጥሬ ገንዘብ መ’ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥ ኦርጅናሉን በጨረታ ፖስታው ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  13. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃና የጨረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  14. የተሳሳተ ስርዝ ድልዝ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጪ ያደርጋል።
  15. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ግለሰብ የአሸነፋቸውን እቃዎች አብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርጫፍ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለበት።
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  17. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30 የሚከፈት ይሆናል።

ማሳሰቢያ 

ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 431 9805 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፣

የአብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *